ቡሩንዲ እና የተመድ ምርመራ ውጤት | አፍሪቃ | DW | 24.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ቡሩንዲ እና የተመድ ምርመራ ውጤት

ስለቡሩንዲ የወጣ አንድ የተመድ ዘገባ፣ የፖለቲካ ታዛቢዎች ከብዙ ጊዜ ወዲህ የጠረጠሩትን ፣ ማለትም፣ በዚችው ሀገር ውስጥ ሆን ተብሎ የሚፈፀም የቁም ስቅል ማሳየት ተግባር እና ካለ ፍርድ ቤት እውቅና የሚፈፀም ግድያ መፈፀሙን አረጋገጠ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:37

ቡሩንዲ

ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ይህንኑ የዘገባ ውጤት ለቡሩንዲን ጉዳይ ይበልጥ ትኩረት መስጠት እንደሚገባው ያሳሰበ ቃጭል አድርጎ ተመልክቶታል።
ስለቡሩንዲ የወጣ አንድ የተመድ ዘገባ፣ የፖለቲካ ታዛቢዎች ከብዙ ጊዜ ወዲህ የጠረጠሩትን ፣ ማለትም፣ በዚችው ሀገር ውስጥ ሆን ተብሎ የሚፈፀም የቁም ስቅል ማሳየት ተግባር እና ካለ ፍርድ ቤት እውቅና የሚፈፀም ግድያ መፈፀሙን አረጋገጠ። ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ይህንኑ የዘገባ ውጤት ለቡሩንዲን ጉዳይ ይበልጥ ትኩረት መስጠት እንደሚገባው ያሳሰበ ቃጭል አድርጎ ተመልክቶታል።

በቡሩንዲ ስለቀጠለው ቀውስ ለመረዳት የተመድ ጠበብት ወደዚችው ሀገር በመሄድ እዚያ 14 ወራት ተቀምጠዋል። በዚሁ ቆይታቸው ወቅት ከመንግሥት እና ከሲቭሉ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ፣ በሀገራቸው ከቤት ንብረታቸው ከተፈናቀሉ ዜጎች እና ወደ ጎረቤት ሀገራት ከሸሹ የቡሩንዲ ስደተኞች ጋር 227 ቃለ ምልልሶችን አካሂደዋል።

የዚሁ ምርመራቸው ውጤት ሰሚዎችን ያን ያህል አላስገረመም፤ ይሁን እንጂ፣ ብዙዎችን ያሳዘነ እና ያስደነገጠ ነው። ምክንያቱም፣ ሕዝብን ማገልገል ያለባቸው የሀገሪቱ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ በዚሁ ግዴታቸው አንፃር፣ ዜጎችን አፍነው ከመውሰድ እና የቁም ስቅል ከማሳየቱ ተግባር እስከ ነፍስ ግድያ ድረስ አልፎ በሄደ ግዙፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ተሳታፊዎችሳይሆኑ እንዳልቀረ ጠቁሞዋል። አሳዛኙ ጉዳይ ግን የቡሩንዲ ቀውስ አሁንም መቀጠሉ እና ቀውሱንም ለማስቆም አንዳችም ርምጃ አለመወሰዱ መሆኑን ከዶይቸ ቬለ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት በቡሩንዲ ምርመራውን የመሩት የተመድ ቡድን ልዩ ተጠሪ እና ክሪስቶፍ ሀይንስ ገልጸዋል።

«ይህ በመጨረሻ የወጣው ዘገባ ካሁን ቀደም የወጡ ሌሎች ዘገባዎች፣ ባለፉት 12 ወራት የነገሩንን፣ ማለትም፣ ሁኔታው እጅግ ሰበበኛ እና እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ነው የደገሙልን። ይህ በመሆኑም ይመስለኛል፣ የተመድ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማንቃት እና በቡሩንዲ የውጭ ተልዕኮ ጣልቃ ሊገባ እንደሚገባ ለማሳመን ሲል በአሁኑ ጊዜ የዘር ማጥፋት የሚለውን ቃል በመጠቀም ላይ ይገኛል።»

በጠመንጃ አፈሙዝ ያረፈ ሰላም
የቡሩንዲ ውዝግብ እና ቀውስ መንስዔው ፖለቲካዊ ነው። የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ፒየር ንኩሩንዚዛ ባለፈው ሀምሌ ወር ለተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን በተወዳዳሪነት እንደሚቀርቡ ባስታወቁበት እጎአ ሚያዝያ 2015 ዓም ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ እቅዳቸውን በመቃወም አደባባይ ወጡ። ያኔ ፖሊስ እና የጦር ኃይሉ ተቃውሞውን በኃይል ተግባር ለመደምሰስ በወሰዱት ርምጃቸው ብዙ ተቃዋሚዎች ነበሩ የተገደሉት። እርግጥ፣ በተቃዋሚዎች እና በፀጥታ ኃይላት መካከል በዚያን ወቅት ታይቶ የነበረው ፍጥጫ መቀነሱን የተመድ ዘገባ አረጋግጦዋል። ይሁን እንጂ፣ በተቃዋሚዎች እና ለመንግሥቱ በማይመቹ ወገኖች ላይ ክትትሉ ተጠናክሮዋል፣ በሀገሪቱ አለ የሚባለው ሰላምም በጠመንጃ አፈሙዝ የተገኘ ነው። ከዚሁ ጎንም የተመድ ጠበብት በቡሩንዲ በጎሳዎች መካከል የሚታየው ክፍፍል እየሰፋ መሄዱን መታዘባቸውን ገልጸዋል። በታዋቂው ለንደን የSOAS ዩኒቨርሲቲ የትልቆቹ ሀይቆች አካባቢ ሀገራት አጥኚ ፊል ክላርክ ይህ የተመድ ቡድን ትዝብትን አስመልክተው ወደ ዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳይቀየር አስጠንቅቀዋል።

«ይህ በመጨረሻ የወጣው ዘገባ ካሁን ቀደም የወጡ ሌሎች ዘገባዎች፣ ባለፉት 12 ወራት የነገሩንን፣ ማለትም፣ ሁኔታው እጅግ ሰበበኛ እና እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ነው የደገሙልን። ይህ በመሆኑም ይመስለኛል፣ የተመድ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማንቃት እና በቡሩንዲ የውጭ ተልዕኮ ጣልቃ ሊገባ እንደሚገባ ለማሳመን ሲል በአሁኑ ጊዜ የዘር ማጥፋት የሚለውን ቃል በመጠቀም ላይ ይገኛል።»

ይሁን እንጂ፣ በተለይ፣ የውጭ ጦር ኃይላትን ወደ ሀገራቸው ለማስገባት ፈቃደኛ እስካልሆኑ ድረስ ፣ ፕሬዚደንት ፒየር ንኩሩንዚዛ እንዳይፈጠር ያሰጋውን የዘር ማጥፋት የሚያከላክል አንድ ዓለም አቀፍ ጦር የአፍሪቃ ህብረት እንደሚታወሰው አንድ የሰላም ተልዕኮ ወደ ቡሩንዲ እንደሚልክ አስታውቆ ነበር። ፊል ክላርክ እንዳሉት፣ ይኸው የአፍሪቃ ህብረት እቅድ እርግጥ የተመድ ተልዕኮን ከማሰማራቱ ሀሳብ ያነሰ ተቃውሞ ብቻ ነበር የገጠመው፤ ይሁን እንጂ፣ በቡሩንዲ አንድ የውጭ ጦር ማሰማራት እስከሚቻል ድረስ ብዙ ወራት ማለፋቸው እንደማይቀር ነው የሚገምቱት።

የመብት ጥሰት ፈፃሚዎቹ ይታወቃሉ።
የቡሩንዲን ውዝግብ ለማብቃት ወታደራዊ ዘዴ ብቻ ሳይሆን ዲፕሎማሲያዊውም ጥረት አስፈላጊ እንሚሆን ፊል ክላርክ አመልክተዋል። ለተመድ ልዩ ተጠሪ ክሪስቶፍ ሄይንስ በመብት ጥሰቱ የተሳተፉትን እና በስማቸው የተጠቀሱትን በኃላፊነት መጠየቅን ወሳኝ አድርገው ይመለከቱታል።

« በቡሩንዲ ለብዙ ወራት አንድ ቡድን አሰማርተን ነበር። የዚሁ ቡድን አባላት መረጃዎችን ሰብስበዋል። የተቃዋሚ ቡድን አባላት የት እንደደረሱ ሳይታወቅ የጠፉበትን ድርጊት በተመለከተ፣ አዘውተረው የሚነሱ 12 ስሞች በእጃችን አሉን። ሌሎች፣ በብዛትም የመንግሥት ባለስልጣናት በቁም ስቅል ማሳየቱ ተግባር ይጠረጠራሉ። ን በተመለከተም ፣ አዎ፣ የበጣም ብዙ ዘገባዎች ዝርዝር አለን፣ በዘገባዎቹ ሁሉ ወቀሳ የቀረበባቸው ሰዎች በተደጋጋሚ በተጠያቂነት እየተጠቀሱ ያሉት ተመሳሳይ ሰዎች ናቸው። »

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለቡሩንዲ ቀውስ ተጨማሪ ትኩረት ይሰጠው ዘንድ ስለዚችው ሀገር ሌሎች ገለልተኛ ምርመራዎች ይደረጉ ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ምርመራውን ያካሄደው የተመድ ቡድን መሪ ክሪስቶፍ ሄይንስ ገልጸዋል።
« በማህበረሰብ ደረጃ በወቅቱ የተጀመረ ጠቃሚ/አስፈላጊ ሂደት አለ። እና ይህ ምናልባት ቡሩንዲን የመሳሰሉ ሀገራትን በተመለከተ ያልተነጋገርንበት ደረጃ ነው። የውጭ ተዋናዮች የቡሩንዲን ሲቭል ማህበረሰብ፣ ማለትም፣ በቡሩንዲ እየታየ ላለው የወቅቱ ከባድ ግጭት ከታችኛው እስከ ከፍተኛው የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ እና ያካባቢ ነዋሪዎችን በማነቃቃት መፍትሔ የሚያፈላልጉትን፣ ባካባቢ ደረጃም የሕዝቡን ስጋት እና ፍርሀት ለመቀነስ የሚጥሩትን የማህበረሰብ መሪዎችን ሊደግፉ የሚችሉበት ሚና አለ። ይህ ዓይነቱ የውጭ ተዋናዮች ሚና ባለፉት 12 ወራት በቡሩንዲ በብሔራዊ ደረጃ የሚታየውን ግጭት ለመቀነስ እና እፎይታ ለማስገኘት ሊረዳ ይችላል።»በቡሩንዲ ከአንድ ዓመት በላይ የሆነው ቀውስ የጀርመን ፌዴራዊ ምክር ቤት፣ ቡንድስታኽ እንደራሴዎችንም አሳስቦዋል። እጎአ በ2015 ዓም አንድ የልዑካን ቡድን መርተው ወደ ቡሩንዲ ተጉዘው የነበሩት በቡንድስታኽ የምሥራቅ አፍሪቃ ጉዳይ ተመልካች ቡድን ሊቀ መንበር ምክር ቤት የተወከሉትክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረት እንደራሴ አኒታ ሼፈርም በሀገሪቱ ሁኔታዎች እየተበላሹ በመሄድ ላይ መሆናቸውን ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል። ሼፈር የቡሩንዲ መንግሥት ማንኛውንም ዓይነት የመብት ጥሰት እንዲያበቃ፣ ጥላቻን የሚያስፋፋ አነጋገርን እና ዛቻ ከማስፋፋት እንዲቆጠብ ተማፅነዋል፤ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ርዳታም በሀገሪቱ ብሔራዊ እርቀ ሰላም የሚወርድበትን ሂደት ለማነቃቃት ወደ ድርሩ ጠረጴዛ እንዲመለስ ጠይቀዋል።
 

ግፊቱን አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ ነው።
የቡሩንዲ መንግሥት ወደ ድርድሩ የማይመለስበት ድርጊት መዘዝ ሊኖረው እንደሚችልም ከቡሩንዲ የጀርመን አምባሳደር ግልጽ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። እንደ አኒታ ሼፈር ገለጻ፣ የጀርመን መንግሥት ከቡሩንዲ ጋር የሚደረግ የልማት ትብብር በየጊዜው መመርመር ይኖርበታል። እንደሚታወሰው፣ የጀርመን መንግሥት ከቡሩንዲ ጋር በልማት ትብብሩ ዘርፍ ያደርገው የነበረውን ስራ አምና በ2015 ዓም በጠቅላላ አቋርጦዋል፤ የአውሮጳ ህብረትም ለቡሩንዲ የሚሰጠውን የበጀት ርዳታም እንዲሁ።

የሀገሪቱን ቀውስ ለማብቃት በቡሩንዲ በአካባቢ ደረጃ ጥረት መጀመሩን ፊል ክላርክ በማሞገስ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን ጥረት ሊደግፍ እንደሚገባ ሀሳብ አቅርበዋል።

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic