በ74ኛዉ የተመድ ጉባኤ የኢትዮጵያ ተሳትፎና የሕዳሴዉ ግድብ    | ኢትዮጵያ | DW | 20.09.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በ74ኛዉ የተመድ ጉባኤ የኢትዮጵያ ተሳትፎና የሕዳሴዉ ግድብ   

ኢትዮጵያ በ74ኛው የተመድ ጉባዔ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ እንደምትሳተፍ ተገለጸ። ይህ የተነገረዉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚቀጥለዉ ሳምንት በኒውዮርክ የሚካሄደውን 74ኛው የተመድ ጉባዔና የኢትጵያን ተሳተፎ እንዲሁም  የታላቁ ህዳሴ ግድብ እንቅስቃሴን በተመለከተ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:42

ኢትዮጵያ በተመድ 74ኛ ጉባዔ በከፍተኛ ደረጃ ትሳተፋለች

ኢትዮጵያ በ74ኛው የተመድ ጉባዔ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ እንደምትሳተፍ ተገለጸ። ይህ የተነገረዉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚቀጥለዉ ሳምንት በኒውዮርክ የሚካሄደውን 74ኛው የተመድ ጉባዔና የኢትጵያን ተሳተፎ እንዲሁም  የታላቁ ህዳሴ ግድብ እንቅስቃሴን በተመለከተ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ነዉ። የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ነብያት ጌታቸዉ አሰግድ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ያለውን ማሻሻያና ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም የክልላዊ፣ የአፍሪካ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባዔ ላይ ንቁ ተሳትፎ ታደርጋለች ብለዋል። የሕዳሴዉን ግድብ በተመለከተ ኢትዮጵያ የአሁን እና የወደፊት ትውልዷን ፍላጎት ለማሳካት በትብብር እና በጋራ ተጠቃሚነት መንፈስ ሉዓላዊ መብቷን በመጠቀም የአባይን ውሃ ማልማቷን እንደምትቀጥል ገልፀዋል። 

ጌታቸዉ ተድላ 

አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ 
 

Audios and videos on the topic