1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በ2016 ዓም የክረምቱ ዝናብ ባስከተለው የተፍጥሮ አደጋ ከ275 በላይ ሰዎች ሞተዋል

ሰኞ፣ ሐምሌ 29 2016

በኢትዮጵያ የተለያዪ ቦታዎች ወቅቱን ጠብቀው የሚከሰቱ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋዎች የሰው ህይወት እያሳጡ ንብረት እያወደሙ አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው።ዶቼቪሊ ያነጋገራቸው በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ በጂዮፊዚክስ ስፔስ ሳይንስ አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር እና አሶሼት ፕሮፌሰር ኤልያስ ሌዊ ኢትዮጵያ 49 % በተፈጥሮ አደጋ የተጋለጠች ነች ይላሉ።

https://p.dw.com/p/4j8fh
ባለፈው ሰሞን የመሬት መንሸራረት አደጋ የደረሰበት የጎፋ ዞና
ባለፈው ሰሞን የመሬት መንሸራረት አደጋ የደረሰበት የጎፋ ዞና ምስል DW

በ2016 ዓም የክረምቱ ዝናብ ባስከተለው የተፍጥሮ አደጋ ከ275 ሰዎች ሞተዋል

ሐምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን፣ በተከሰቱ ሁለት የመሬት መንሽራተት አደጋ ምክናየት ከ257 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፎል ።ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ/ም በአማራ ክልል ፣ በደሴ ከተማ አስተዳደር ፣ የተፈጠረ የመሬት መንሸራተት መጠነኛ ጉዳት አድርሷል።አደጋው  በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት ባይኖርም  ቤቶች ፈርሰዋል መንገዶች ተሰነጣጥቀው  መንገደኞች ተለዋጭ  መንገድ  እንዲጠቀሙ ተገደዋል።የመሬት ናዳው በመቶዎች የሚቆጠሩትን ከቄዬአቸው አፈናቅሏል

ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ወላይታ ዞን በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ12 ሰው ህይወት ሲያልፍ ፣ በ1 ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶበታል  የአካባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው  እንድፈናቀሉ ተገደዋል ።እንድሁም በሲዳማ ክልል፣ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የውሀ ሙላት አደጋ የሞቱ ዜጎች ቁጥር ከ11 አልፎል።

የበቡራ ወረዳ ወንዝ ሞልቶ ከመስመር  ውጭ በመፍሰስ በአካባቢዉ ያሉ ቤቶች ፍርሰው የ 2 ልጆች ህይወት  ተቀጥፏል። በኢትዮጵያ የተለያዪ ቦታዎች ወቅቱን ጠብቀው የሚከሰቱ የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋዎች  የሰው ህይወት እያሳጣ ንብረት  እያወደሙ አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው።ዶቼቪሊ ያነጋገራቸው በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ በጂዮፊዚክስ ስፔስ  ሳይንስ አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር እና አሶሼት ፕሮፌሰር ኤልያስ ሌዊ ኢትዮጵያ 49 % በተፈጥሮ አደጋ የተጋለጠች ነች ይላሉ።

በጎፋው የመሬት መንሸራተት ከመሬት በቃች የተቀበሩ ሰዎች ፍለጋ
በጎፋው የመሬት መንሸራተት ከመሬት በቃች የተቀበሩ ሰዎች ፍለጋ ምስል MICHELE SPATARI/AFP


ለጎፋ የአደጋ ሰለባ ቤተሰቦች የሚደረገው የርዳታ ሁኔታየተፈጥሮ አደጋዎች መጠ-ነሰፈ መነሻ አለ ያሉት ምሁር እሳቸው የሚመሩት ተቋም እና ሌሎች በዘርፉ ላይ የሚሰሩት ተቀዋማት ሀገሪቱ ያለባትን የተፈጥሮ አደጋ ስጋት ጥናት ለሚመለከተው ክፍል በየጊዜው  መቅረባቸውን ይናገራሉ። የመሪት መናድም የመሪት መንቀጥቀጥ እና ሌሎችም የተፈጥሮ አደጋ  በሚከሰትበት ጊዜ ህብረተሰቡ ምን ማድረግ እንዳለበት ግንዛቤ ሊሰጠው እና  በየትምህርት ቤቶች ሊማረው ሊለማመደው  ይገባል ብለዋል

ሀና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ