በፖድካስት ጀርመንኛ ይማሩ | Podcasting & Feeds | DW | 22.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

Podcasting & Feeds

በፖድካስት ጀርመንኛ ይማሩ

በጉዞ ላይ ሆነው ከዶቼ ቬለ በነፃ በሚያገኙት ፖድካስ አማካኝነት የጀርመንኛ ችሎታዎን ያዳብሩ! ዕለት ከዕለት ከሚጠቀሙበት ጀርመንኛ አንስቶ፣ እስከ በዝግታ የሚነበቡ ዜናዎችና ሙሉ የትምህርት ክፍሎችን ያገኛሉ ፤ ይዘዙና ይማሩ!

የፖድካስት የምልክት ምስሎች

ከ DW-WORLD ጋር ምንጊዜም ጀርመንኛ ይማሩ!

ፖድካስት የሚለው ቃል የተፈጠረው "iPod" ከሚለው የአፕል ጅርጅት ፤ የ MP3 ማጫወቻ ልዩ ምልክት እና - "broadcasting" ከሚለው ሌላ ቃል ነው። በቀጥታ ሲተረጎም « ሬዲዮ ለ አይፖዶች » የሚለውን ይመስላል። ይህ ደግሞ የድምፅና የምስል ወቅታዊና የዘውትር ዘገባዎች ያካትታል። እነዚህን ዝግጁቶችም በቀጥታ በ DW-WORLD.DE ድረ ገፅ ላይ ወይም እንደ iTunes የሙዚቃ መደብር የመሳሰሉት ከፖድካስት ዝርዝሮች ላይ ማዘዝ ይችላሉ።

በየጊዜው፤ በየትም ቦታና በነፃ

በፈለጉበት ሰዐት የዶቸ ቬላ የድምፅና የምስል ዝግጁቶችን በፖድካስት አማካኝነት ጠርተው መመልከትና ማዳመጥ ይችላሉ። በተጨማሪም የግልዎን የድምፅና ቪዲዮ ዝግጅቶች መርጠው (የ ግል ፖድካስት ) ሊያቀናብሩ ይችላሉ። እነዚህንም ዝግጅቶች በማንኛውም ቦታ ሲንቀሳቀሱ ማዳመጥ ይቻላል። ለምሳሌ በ MP3-ማጫዎቻዎች።

ለዛ ደግሞ ግዴታ ማጫዎቻዎ iPod መሆን የለበትም።

አመቺው ሁኔታ በእጅዎ ነው ያለው። የት፣መቼ የትኛውን ርዕስ ማድመጥ እንደሚፈልጉ ምርጫዎን መወሰን ብቻ ነው። የዶቸ ቬለ የድምፅና የምስል ዝግጅቶች (የፖድካስት አቅርቦ) ነፃ ናቸው።

አካሄዱ እንዲህ ነው

ፖድካስቱን ለማዘዝ ኢንተርኔትና ትክክለኛ ሶፍት ዌር ያስፈልገዎታል። በፖድካስቱን መርሀ ግብር ማለትም (Podcasting-Clients) የሚፈልጉትን የድምፅ ወይም የምስል ቅንብር አይነት ከ DW-WORLD.DE ማዘዝና የመረጡትን ክፍሎች በ MP3 ማጫዎቻዎት ላይ መጫን ይችላሉ። ለድምፅና ምስል ቅንብሮች (ፖድካስትቶች)Feed-Technology የሚባል ቴክኖሎጂ አላቸው። Podcast-Feed ዉስጥ Tags የሚባሉ ማለትም ወደ ድምፅ መዝገቦች የሚመሩ ገፆች አሉ። የ RSS-Feeds ን አድራሻ ፖድካስትዎትን ካመቻቹ በኃላ Podcasting-Client ላይ ያስገቡ። በኋላም የሚፈልጉትን ዝግጅት በፖድካስት መልክ ካዘዙ በኋላ ወዲያው በቀጥታ መልዕክቱ ወደ MP3 ማጫወቻዎ መላክ ይጀምራል።

Podcasting-Client ዎ ሁሉንም በቅደም ተከተል ያጠናቅቃል። ወቅታዊና አዲስ የሆኑትን ተከታታይ ክፍሎች ኮምፒተርዎ ወይም MP3 ማጫወቻዎ ላይ ይጭናል። Podcasting-Client ን የጀመረው iPodder ነው። ግን ሌሎች እንደ iTunes የመሳሰሉ አቅራቢዎችም አሉ። ( ከታች ያሉትን ገፆች ይመልከቱ) ከነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ፕሮግራሞች በነፃ ናቸው።

አቅርቦቱ በቂ ነው

ዶቸ ቬለ እንደ መጀመሪያ ህጋዊ የራዲዮ ማሰራጫነቱ እ ኤ አ ከ 2004 የአሜሪካ ፕሮዜዳንታዊ ምርጫ ጀምሮ ዝግጅቶቹን በፖድካስት መልክ ማቅረብ ጀምሯል። ቀደም ሲል በድምፅ የሚተላለፉ መልዕክቶች ብቻ ነበሩ በፖድካስት መልክ ማግኘት የሚቻለው አሁን ግን የምስል ፖድካስቶች ይበልጥ ተወዳጅነትን አትርፈዋል። እናም አሁን የ DW-WORLD.DE ድረ ገፅ ላይ ከ 50 የበለጡ የድምፅና ቪዲዮ ፖድካስቶች ማዘዝና ኮምፒተርዎ ላይ መጫን ይችላሉ።

አቅርቦታችን ከ ራዲዮና ከቴሌቪዥን ዝግጅቶች አልፎ የቋንቋ ትምህርቶችና ልዩ ልዩ አርዕስቶች ላይ የሚያተኩሩ የዶቼ ቬለ ዝግጅቶችን ያካትታል።

DW.COM