በፈቃዱ ኃይሉ በዋስትና እንዲለቀቅ ተወሰነ | ኢትዮጵያ | DW | 21.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በፈቃዱ ኃይሉ በዋስትና እንዲለቀቅ ተወሰነ

የዛሬው ችሎት በፍቃዱ የተከሰሰበት አንቀፅ የዋስትና መብት የማያስከለክለው መሆኑንና ውጭ ሆኖ ቢከራከር የሽብር ተግባሩን ሊቀጥልበት ይችላል ብሎ አቃቤ ህግ አስረጂ ባለማቅረቡ በፈቃዱ በዋስ ወጥቶ ጉዳዩን እንዲከላከል ፈርዷል ።ዛሬ ያስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቤት 19ነኛ ወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ የኢንተርኔት ፀሃፊ በፍቃዱ ኃይሉ በ20 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቅ ወሰነ።በፍቃዱ ህገ መንግሥታዊ ስርዓቱን ለመናድ በኃይል ተንቀሳቅሰዋል በሚል ወንጀል ተከሰው ከታሰሩት የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ፀሀፍት ሁለተኛው ተከሳሽ ነበር ።በዚሁ ወንጀል ተከሰሰው ከታሰሩት 8 ፀሀፍት መካከል የ4ቱ ክስ ባለፈው ሐምሌ ፣ በሌለችበት የተከሰሰችውን የሶልያና ሽመልስና ለአንድ ዓመት ከ6 ወር በእርስ ላይ የቆዩትን የ3ት ፀሀፍት ክስ ደግሞ ባለፈው አርብ ፍርድ ቤት አንስቶላቸዋል ። የበፍቃዱ የአሸባሪነት ክስ ተሰርዞ አመጽን በማነሳሳት ወንጀል እንዲቀየር ፍርድ ቤቱ ባለፈው አርብ ወስኖ ነበር ። የዛሬው ችሎት በተከሳሽ ጠበቃ የቀረበውን የዋስ መብት አቤቱታና የአቃቤ ህግ ምላሽ ካዳመጠ በኋላ በፍቃዱ የተከሰሰበት አንቀፅ የዋስትና መብት የማያስከለክለው መሆኑን አስታውቋል ። ውጭ ሆኖ ቢከራከር የሽብር ተግባሩን ሊቀጥልበት ይችላል ብሎ አቃቤ ህግ አስረጂ ባለማቅረቡ በፈቃዱ በዋስ ወጥቶ ጉዳዩን እንዲከላከል ፈርዷል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic