በፀረ-ሽብር ሕግ የተከሰሱ የ 77 ሰዎች ችሎት  | አፍሪቃ | DW | 06.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

በፀረ-ሽብር ሕግ የተከሰሱ የ 77 ሰዎች ችሎት 

የግንቦት ሰባትና የኦነግን አላማ ይዘዉ ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉና በፀረ ሽብር ሕጉ የተከሰሱ 77 ሰዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። በ19 ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የዋለዉን የፍርድ ሂደት የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ተከታትሎታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:33

«ክሱ የተብራራ አይደለም ተብሎአል»


የግንቦት ሰባትና የኦነግን አላማ ይዘዉ ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉና በፀረ ሽብር ሕጉ የተከሰሱ 77 ሰዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተከሳሾቹ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ተፈረጁ ከተባሉት ድርጅቶች ጋር ኤርትራ ሄደዉ ወታደራዊ ስልጠና በመዉሰድና ሀገር ዉስጥ በመግባት የሽብር ተግባር ሲፈፅሙ ተገኙ ተብሎ በተለያዩ እስር ቤት ተይዘዉ ከቆዩ በኋላ ፍርድ ቤት መቅረባቸዉ ተመልክቶአል። በ19 ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የዋለዉን የፍርድ ሂደት የተከታተለዉ ወኪላችንን  በስልክ ጠይቀነዉ ነበር።     
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

Audios and videos on the topic