በጥንታዊት ኢትዮጽያ የቀጭኑ ሽቦ መገናኛ | ባህል | DW | 12.11.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

በጥንታዊት ኢትዮጽያ የቀጭኑ ሽቦ መገናኛ

አሎ አሎ ማዞርያ፣ ማዞርያ ነዉ?..... ይባል ነበር አሉ፣ ባገራችን እንዲህ እንደ አሁኑ ሞባይል በሚባለዉ በኪስ በሚያዘዉ የጀታዉ ስልክ ሳይገባ። አሁንማ በተንቀሳቃሹ ስልክ እየተደዋወልን፣ ደግሞ እዚህ መሆኔን ማነገረህ መባባል ጀምረናል።

የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ

የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ

የዛሪ 165 አመት ግድም በአለማችን ብቅ ያለዉ ቴክኖሎጂ በአሁን ወቅት በአለም ዙርያ እየሰጠ ያለዉ ግልጋሎት በጣም የሚደነቅ አድርጎታል። በተንቀሳቃሹ ስልክ በሞባይል የተፈለገዉን ሰዉ ማግኘት አልያም የጹሁፍ መልክት ሁሉ ማስተላለፍ ተችሎአል። አፍሪቃ የሞባይል ስልክ መናሃርያ ሆናለች የሚሉ መጣጥፎችም በምዕራባዉያኑ አለም ጋዜጦች አበይት ርእስ ሆኖ መዉጣት ከጀመረ ሰንበበት አለ። በአዉሮፓ የሚኖሩ ኬንያዉያን በኬንያ የሚኖሩና የባንክ መዝገብ ለሌላቸዉ ዘመዶቻቸዉ ገንዘብ የሚያስተላልፉት በጀታ ስልካቸዉ መልክት በማስተላለፍ ነዉ፣ በኬንያ ያለዉ የተንቀሳቃሽ ስልክ ድርጅት ይህንን አገልግሎት መስጠት ጀምሮአል የሚለዉ የሳምንቱ ትኩሱ ስልክ ነክ ዜናም ነበር። በአገራችን ስላለዉ ስለ ቀጭኑ ሽቦ የስልክ አመጣጥ ታሪክ ከጥንታዊዉ ባህል እና የኑሮ ዘይቤ ጋር በማጣጣም የባህል መድረኩ ሊያሳየን ተዘጋጅቶአል መልካም ቆይታ።