በግሪክ ሰደተኞች የሚደርስባቸው በደል | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.03.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

በግሪክ ሰደተኞች የሚደርስባቸው በደል

የአውሮፓ ህብረት አባል በሆነችው በግሪክ በውጭ ዜጎች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት እየተባባሰ በመሄድ ላይ ነው ። የጥቃቱ መንስኤና ችግሩን ለመቋቋም የሚወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

default

ካለፉት 3 ዓመታት ወዲህ በገንዘብ ቀውስና በምጣኔ ሃብት ክስረት ደጋግማ የምትነሳው ግሪክ ለውጭ ዜጎች የምትመች ሃገር አልሆነችም ። ክቅርብ ዓመታት አንስቶ መዲናይቱን አቴንስን ጨምሮ በሌሎችም ዋና ዋና ከተሞች የሚፈፀሙ ዘረኝነትን መነሻ ያደረጉ ወንጀሎች እየተበራከቱ ነው ።  ወደ 18 የሚሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ባካሄዱት ምዝገባ ከዚህ ዓመት ጥቅምት እስከ ታህሳስ ወር ባለው ጊዜ ብቻ 63 ዘረኝነትን  መነሻ ያደረጉ ጥቃቶች ደርሰዋል ። ከነዚህም በ 51 ዱ ከ 1 በላይ የሆኑ ሰዎች ተሳትፈዋል ። ዶቼቬለ የአማርኛው ክፍል ያነጋገራቸው በግሪክ የተባበሩት መንግሥታት የሰደትኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር የህዝብ ግንኙነት መኮንን ኬቲ ኬሃይእዮይሉ ችግሩ ግዙፍ መሆኑንና  አሁን አፍጦ  መውጣቱን ይናገራሉ ።

 « ብዙ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን በጥቁር ልብሶች ሽፍነው ስዎችን በአውቶብስ ጣቢያዎች ያስቆማሉ ። ወይም በውሾች ያሸማቅቋቸዋል ። ከዚያም ጥቃት ያደርሱባቸዋል ። በነዚህ 3 ወራት እነዚህ 63 ጥቃቶች ነበሩ ። ይሁንና ይህ የተቆለለው ችግር ጫፍ ላይ የሚደርስ አይደለም ። »

Flüchtlinge in Griechenland

እጅግ ብዙ ያልተመዘገቡ ወይም የማይታወቁ ዘረኝነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ይደርሳሉ ። ከበደለኞቹ አብዛኛዎቹ ህጋዊ ሰነድ የሌለቸው ስደተኞች በመሆናቸው የመታሰር ወይም የመባረር እጣ እንዳይገጥማቸው የደረሰባቸውን ጥቃት ለፖሊስም ሆነ ለሚመለከተው አካል ማመልከት ይፈራሉ ። አንድ ማነነቱ ያልተገለፀ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ብቻ በፖሊስ ላይ ያለውን ቅሪታ አመልክቷል ። UNHCR ም ሆነ የግሪክ ብሔራዊ ሰብዓዊ መበት ኮሚሽን የግሪክ ዜግነት ያለው ትወልደ ኢትዮጵያዊ ዋና ከተማዋ አቴንስ ውስጥ መንገድ ላይ ጥቃት እንደደረሰበት ከማናገር ውጭ ዝርዝሩን  ከማሳወቅ ተቆጥበዋል ። በዚህ መልኩ በሰደትኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት  እንዲባባስ  አስተዋፅኦ ካደረጉት ውስጥ የመንግሥት አቅም ማነስ  አንዱ ነው እንደ ሚሲ ኬሃይእዮይሉ ። ከዚሁ ጋርም ሃገሪቱ አሁን የምትገኝበት ሁኔታም ተጨማሪ ምክያት ነው ይላሉ ።

Afghanische Flüchtlinge in einem Flüchtlingslager in Griechenland

« ግሪክ እነዚህን በብዛት የሚጎርፉ ስደተኞች ማስተናገድ የሚያስችል ትክክለኛ የአሰራር መዋቅርም ሆነ የማቆያ ስፍራ የላትም ። በዚህ የተነሳም በአንድ በኩል አንዳንዶች ያለምንም ድጋፍ እና ጥበቃ በመዲናይቱ አቴንስ ወድቀዋል ። በሌላ በኩል ደግሞ የግሪክ ማህበረሰብ ከዚህ ቀደም ያልተጠበቀ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ውስጥ ነው ያለው ። አንዳንዱ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲፈጠር ማመካኛ ያደርጉታል ። በሌላም በኩል ብዙ ፖለቲከኞችም በቅርቡ በሚካሄደው ምርጫ ምክንያት ህዝብን የሚያነሳሳና የውጭ ዜጎች እንዲጠሉ የሚያደርግ ቅስቀሳ ይለፍፋሉ ። »

በደቡባዊ ምሥራቅ አውሮፓ በኩል የአውሮፓ ህብረት ድንበር የሆነችው ግሪክ በረካታ ሰደትተኞች ከሚጎርፉባቸው አገራት አንዷ ናት ። የተባበሩት መንግሥታት የሰደተኞች  ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር በእንግሊዘኛው ምህፃር UNHCR እንደሚለው በጎጎሮሳውያኑ 2011 ብቻ መንግሥት ህገ ወጥ የሚላቸው ቁጥራቸው 99 ሺህ የሚሆን ስደተኞች ግሪክ ገብተዋል ። ከዚያ በቀደመው እጎአ በ2010 ደግሞ 132 ሺህ ነበሩ ድንበር ተሻግረው ግሪክ የደረሱት ። በዚህ ሳቢያ ከአቅሟ በላይ በሰደተኞች የተጨናነቀችው ግሪክ የውጭ ዜጎች ፍዳቸውን የሚቆጥሩባት ሃገር ሆናለች ። በውጭ ዜጎች ላይ ጥቃት በመፈፀም ተግባር የተሰማሩት ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህፃናት ጭምር መሆናቸውን UNHCR ም ሆነ የግሪክ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ይናገራሉ ። በአንዳንድ ጥቃቶች የግሪክ ፖሊስ በተባባሪነት ሲከሰስ አንዳንዴም ከጥቃቶች በሰተጀርባ አለበት የሚሉ ስሞታዎችም ይደመጣሉ ። የግሪክ ብሔራዊ የሰበዓዊ መብት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ኮስቴስ ፓፓዮዋኖ ለዶቼቬለ አማርኛው ክፍል በሰጡት አሰተያየት ፖሊስን ዘረኛ ቡድኖችን በዝምታ በማለፍ ነው የወቀሱት ።

« ፖሊስ ከጥቃቶቹ በሰተጀርባ አለ ማለት አልችልም ።  ማለት የምችለው ግን ፖሊስ በግልፅ ዘረኝነትን መሠረት ያደረጉ ወንጀሎችን የመከላከል ፍላጎት አያሳይም ። አንዳንድ ጊዜ ዘረኛ ቡድኖችን እጅግ የሚታገስ ነወ የሚመስለው ። »

በነዚህ ምክንያቶች UNHCR ና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በጋራ በጀመሩት ሰርቶ ማሳያ በግሪክ በስደተኞች ላይ የሚደርሱ ወንጀሎችን ካለፈው ጥቅምት አንስቶ እስከ ታህሳስ ድረስ ሲመዘግቡና ሲከታተሉ ቆይተዋል ። ዓላማውም ኬሃይእዮይሉ እንደሚሉት መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲስጥ ማድረግ ነው ።

«የምዝገባው  ሃሳብ መንግሥት ከዘር ጥላቻ ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን መመዝገብ የሚያስችለውን የጋራ ስርዓት እንዲዘረጋ  ለመጠየቅ ነው ።   ይህ ምናልባትም በፍትህ ሚኒስቴር አማካኝነት ሊሆን ይችላል ። እነዚህ ሰዎች በአግባቡ እንዲያዙ ና ችግር ሲደርስባቸውም ወዴት መሄድ እንዳለባቸው እንዲያውቁ ለማድረግ ነው ።

ሰለሆነም  ምንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የተጀመረውን ትገባር የግሪክ መንግሥት የመቀጠሉ አስፈላጊነት አያጠያይቅም ይላሉ ፓፓዮዋኖ ። መንግሥት በዘረኛ እንቅስቃሴዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድም ያሳስባሉ ።

« በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህን መረጃዎች የመሰብሰቡ ሃላፊነት የግሪክ ባለሥልጣናት ነው ። እኛ ያለ ተጨማሪ ገቢና የሰው ሃይል ለዘላለም ልናከናውን የምንችለው አይደለም ። እጅግ አስፈላጊ የሆነው የዚህ መርጃ እጥረት አለ ። ዘረኝነትን መነሻ ያደረጉ ወንጀሎችን ማሰባሰቢያ መዋቅር የለም ። ሌላው በዚህ ወቅት ላይ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ምርጫ ይካሄዳል ፤ በዚህ ወቅት ላይ ዘረኝነትን መነሻ ያደረጉ  ወንጀሎችና ዘረኛ ንግግሮችን መታገሥ አይገባም በተለይም ጥቃትም በዝምታ ሊታለፍ አይገባም ። »

ፓፓዮዋኖ ሁኔታው ወደፊት ይባባሳል የሚል ስጋት ነወ ያላቸው ።

« አፍቃሪ ናዚዎች መኖራቸው ብቻሳይሆን ይግሪክን ህዝብ ለማዳን በሚል መንቀሳቀሳቸው ያሳሰበናል ። ሁሉም ባይሆን የተወሰነው በጎዳናዎች ላይ ከሚታይ አመፅ ጋር እየኖረ ነው ።እናም እየተባባሰ ነው ። ክዚህም ይብሳልምብለን እንሰጋለን ። »

ታዲያ ለዚህ ሁሉ ችግር መፍትሄዎ ምን ይሆን የUNHCR ኬሃይእዮይሉ

« የግሪክ መንግሥት በነሐሴ 2010 ለጥገኝነት አሰጣጥ ስርዓት ማሻሻያ ፣   ያወጣውየድርጊት መርሃ ግብር በተቻለ ፍጥነት ተግባራዊ መሆኑ አሰፈላጊ ነው ።ይህ ጥገኝነት,ሊስጣቸው የሚገባና ይህም  የማይገባቸውን ለመለየትና ድጋፍ ወይም ጥበቃ የማያስፈልጋቸውን ለማወቅ ና በዚህ ውስጥ የማያካተቱትን ለመለየትን የሰደተኞችም ጎርፍ ስረዓት ለማስያዝ ይረዳል >

ኬሃይእዮይሉ መፍርሄ ያሉት ይህ ሲሆን የግሪክ ብሔራዊ ሰብዓዊ መበት ኮሚሽን ደግሞ

ከመንግሥት በኩል ችግሩን የማቃለል ፍላጎት መታየት አለበትይላሉ ።

Internierungslager in Griechenland

« በአጭር ጊዜ ውስጥ ባለሥልጣናት ችግሩን የማቃለል ፍላጎት ሊያሳዩ ይገባል ። እነዚህን አፍቃሪ ናዚ ቡድኖች ለመቆጣጠር ክሶችን መመረመር ይኖርባቸዋል ። ፖሊስ ላይ ክስ ሲኖርም ምንም ዓይነተ ያለመከሰስ መብት እንደማይኖር ግልፅ ምልክት ሊኖር ያስፈልጋል ። በብዛት የሚጎርፉትን ስደተኞች ለማስተናገድም የተሻለ እቅድ ያስፈልጋል ። »

በUNHCR ም ሆነ በግሪክ ሰብኦዊ መበት ኮሚሽን እምነት የህብረቱ ድንበር የሆኑት ስፔይን ግሪክ ናኢጣልያ በደበሊኑ ስምምነት ምክንያት የተሸከሙትን ስደተኞችን የማስተናገድ ከባድ ሃላፊነት የአውሮፓ ህብረትም መጋራት ይገባዋል ።  

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 27.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14T5g
 • ቀን 27.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14T5g