ኤኮኖሚ
የስኳርና የደም ግፊት ሕመም መድኃኒቶች ማግኘት ፈታኝ ሆኗል
ረቡዕ፣ መጋቢት 12 2010ማስታወቂያ
አዲስ አበባ በሚገኙ ስምንት የመድኃኒት መደብሮች ለስኳር ሕሙማን የሚታዘዘው ሜትፎርሚን የተባለ መድሐኒት አይገኝም። ለደም ግፊት የሚታዘዘው ኒፊዲፒን የተባለ መድኃኒት ማግኘትም ይቸግራል። ለዚህ ዘገባ በ10 የመድኃኒት የመድሐኒት መደብሮች በመደወል ለማጣራት እንደሞከርንው ከሜትፎርሚን እና ኒፊዲፒን በተጨማሪ የተለያዩ መድኃኒቶች እጥረት በገበያው ላይ መኖሩን ለመታዘብ ችለናል። በመድኃኒት ገበያው ላይ የሚታየውን እጥረት የታዘቡ የፋርማሲ ባለሙያዎች እና የመድኃኒት መደብር ባለቤቶች ችግሩን ቢያረጋግጡም በይፋ ለመናገር ግን አይሹም። ሁሉም ግን አይደሉም። ላለፉት አራት ገደማ አመታት የመድሐኒት እጥረት ይታይ እንደነበር የሚናገሩት የፋርማሲ ባለሙያው አቶ ጸጋዬ ገብረየስ የአሁኑ ለየት እንዳለ ያስረዳሉ። ምክንያቱ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ነው።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ