በግልገል ጊቤ ግድብ ላይ ተቃውሞና የመብራት ኃይል መግለጫ፣ | ኢትዮጵያ | DW | 21.05.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በግልገል ጊቤ ግድብ ላይ ተቃውሞና የመብራት ኃይል መግለጫ፣

የዓለም አቀፉ የወንዞች ተቋምና ፣ ከማሊ፣ ከኬንያ፣ ከዩጋንዳና ከቶጎ የተውጣጡ ማኅበራዊ ተቋማት፣ በኦሞ ወንዝ ላይ የሚገነባው ግድብ ፣ ለአካባቢው ህዝብና ለተፈጥሮ አካባቢ ጠንቅ ነው ሲሉ ተቃውሞ ማቅረባቸው ተነገረ።

default

ግድብ፣

ይህን ተቃውሞአቸውን ያሰሙት ፣ በቅርቡ፣ የአፍሪቃ ልማት ባንክ፣ ዳካር፣ ሴናጋል ውስጥ ዓመታዊ ጉባዔውን ባካሄደበት ወቅት እንደነበረ ታውቋል። የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ድርጅት፣ እንደሚነገረው፣ በ 17 ቢልዮን ብር እያስገነባው ያለውና 1,870 ሜጋ ዋት ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጨው የግልገል ጊቤ ቁ 3፣ ፕሮጀክት፣ 32 ከመቶ ሥራው ተጠናቋል ሲል ድርጅቱ አስታውቋል። የመብራትኃይሉ ድርጅት፣ ግድቡ፣ ለአካባቢው ኑዋሪዎችና ለብዝኅ-ህይወት አደጋ ይኖረዋል በማለት ፣ የውጭ አበዳሪዎች፣ የሚሰጡትን ብድር ለጊዜው አግደዋል ተብሎ የተወራው ስህተት ነው ሲል ለ ዶቸ ቨለ ግልጿል። አበበ ፈለቀ፣ ከዋሽንግተን ዲ ሲ፣እንዲሁም ታደሰ እንግዳው ከአዲስ አበባ ተከታዮቹን ዘገባዎች አጠናቅረዋል።

ተክሌ የኋላ፣

ሒሩት መለሰ፣