በጋና የተቃዋሚው ፓርቲ ዕጩ አኩፎ አዶ ማሸነፍ | አፍሪቃ | DW | 10.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

በጋና የተቃዋሚው ፓርቲ ዕጩ አኩፎ አዶ ማሸነፍ

በጋና የዋነኛው የተቃዋሚው፣ አዲሱ የአርበኞች ፓርቲ» በምህጻሩ የ« ኤን ፒ ፒ« ዕጩ ናና አኩፎ አዶ ባለፈው ረቡዕ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድል ተቀዳጁ። የሀገሪቱ አስመራጭ ቦርድ እንዳስታወቀው፣ የ72 ዓመቱ አኩፎ አዶ 53.85% በሆነ ድምጽ የገዢውን የብሄራዊ ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪና የጋናን ፕሬዚደንት ጆን ድራማኒ ማህማን አሸንፈዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:40
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:40 ደቂቃ

ስዩሙ የጋና ፕሬዚደንት ናና አኩፎ አዶ

44,4% ድምጽ ብቻ ያገኙት ማሀማ ሽንፈታቸውን ተቀብለዋል። እጎአ በ2008 እና 2012  ተወዳድረው ያልቀናቸው አኩፎ አዶ አሁን በ3ኛ ሙከራ ለዚሁ ስልጣን በቅተዋል።  በዚህም በሀገሪቱ የተካሄደው እና በተፎካካሪ ዕጩዎች መካካከል ብዙ መወቃቀስ የታየበት ምርጫ ፍጻሜ አግኝቷል።  
በመዲናይቱ አክራ ማዕከል የሚኖሩት ኦሴይ ክዋኩ አኒሜዱ አኩፎ አዶ ካሁን በፊት የገዢው « ኤን ዲ ሲ» ጠንካራ  ሰፈር በሆነው በዚሁ አካባቢ የብዙኃኑን ድምጽ በማግኘታቸው እና ምርጫውን በማሸነፋቸው እንደረኩ ገልጸዋል። እኒሁ እጎአ ከ1970 እስከ 1972 ዓም የጋና ፕሬዚደንት የነበሩት የኤድዋርድ አኩፎ አዶ ልጅ  የሆኑት ስዩሙ ፕሬዚደንት አኩፎ አዶ የሚመሩት መንግሥትም ከተሰናባቹ የተሻለ እንደሚሆን ተስፋ አድርገዋል።


« ካሁን ቀደም ስልጣን ላይ የበነረው እና አሁን እንደገና ወደ ስልጣን የመጣው ፓርቲያቸው ካለፉት ተሞክሮዎቹ ትምህርት እንደቀሰመ እና የተሻለ ስራ እንደሚሰራ ተስፋ አለኝ። »
የፕሬዚደንታዊው ምርጫ ውጤት ብዙው የጋና መራጭ ሕዝብ  ከስምንት ዓመት «ኤን ዲ ሲ» አመራር በኋላ ለውጥ መፈለጉን እንዳረጋገጠ አኒሜዱ ገልጸዋል። በምህጻ፣ ፕሬዚደንት ማሀማ መንግስት እየተዳከመ ለሄደው የ ጋና ኤኮኖሚ እና ለግዙፉ ስራ አጥነት መፍትሄ ማስገኘት አልቻለም።
« የጋናን ሕዝብ ቁጥር እድገት ስንመለከት በያመቱ ወደ 300,000 የሚጠጉ ወጣቶች ወደ ስራው ገበያ ይመጣሉ። የግሉ ዘርፍም ሆነ መንግሥት ይህን ስራ ፈላጊ የሚያስገባበት በቂ የስራ ቦታ አልፈጠሩም። ወጣቱን ምን ልትለው ትችላለህ? በአሁኑ ጊዜ በወላጆች እና በተማሪዎች ዘንድ ቅሬታው ትልቅ ነው። »

በ2011 እና 2015 መካከል ኤኮኖሚው እድገት በ10% ነበር የቀነሰው።

ተሰናባቹ ፕሬዚደንት ጆን ድራማኒ ማሃማ

ተሰናባቹ ፕሬዚደንት ጆን ድራማኒ ማሃማ

በመሆኑም አዲሱ ፕሬዚደንት ለዚሁ ችግር ባስቸኳይ መልስ መስጠት ይኖርባቸዋል፣ እንደ አቤ ግምት። በምርጫ ዘመቻ ወቅት በ26 ቱ የምርጫ አካባቢዎች አንድ ፋብሪካ ለመክፈት እና የኤኮኖሚ ተሀድሶ ለማነቃቃት  ቃል ገብተዋል። ሀገራቸው ጋምም ሁሌ ጥሬ አላባ ወደ ውጭ የምትልክ ሀገር ብቻ መሆን እንደሌለባት፣ ከዚሁ ጎንም ምርቷን ወደ ኢንዱስtri ምርት መለወጥ የምትችልበትን አቅም መፍጠር እንዳለባት አስታውቀዋል። ከዚህ በላይ ግን በምርጫ ዘመቻ ወቅት የተፈጠረውን የመከፋፈል ሁኔታ የማብቃት ትልቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው አንድ የሀገሪቱ ዜጋ አሳስቦዋል።
«ለቀጣዩ የጋና ፕሬዝዳንት የማስተላለልፈው መልዕክት ህብረት እንደሚያስፈልገን ነው ። ከምርጫ በኋላ ውጤቱን መሠረት አድርገው ሰዎች ደስተኛ አይሆኑም ። ስለዚህ የሚመረጠው ሁላችንንም አንድ የሚያደርግ መሆን አለበት ። ከተከፋፈልን እንወድቃለን አንድ ከሆን ደግሞ እንቆማለን ።»

አርያም ተክሌ/ካትሪን ጌንስለር

ኂሩት መለሰ

 

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች