1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጋምቤላ ክልል በበነዋሪዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መጨመራቸው

ዓርብ፣ ሰኔ 14 2016

በጋምቤላ ክልል በግለሰቦች ላይ የሚደርስ ጥቃት እና ግድያ መበራከቱን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገለፁ፡፡ ባለፈው ሳምንት አርብ ምሽት አንድ ግለሰብ ላይ በስለት ጥቃት ደርሶ ህይወቱ ማለፉን፤እንደዚሁም እሁድ ዕለት በአንድ ግለሰብ ላይ ጥቃት መድረሱን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡በሞተር እና በባጃጅ የታገዘ ጥቃትም ለነዋሪው ስጋት ሆኗል።

https://p.dw.com/p/4hLfo
68694032የጋምቤላ ክልል ርዕሰ ከተማ ግምቤላ አደባባዮች አንዱ
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ ከተማ ግምቤላ አደባባዮች አንዱ ምስል Negassa Desalegn/DW

በጋምቤላ ክልል በነዋሪዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መጨመራቸው

በጋምቤላ ክልል በግለሰቦች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ግዲያ መበራከቱን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቁ፡፡ ባለፈው ሳምንት አርብ ምሽት አንድ ግለሰብ ላይ በስለታማ መሳሪያ ጥቃት መድረሱን ህይወቱ ማለፉን፤ እንደዚሁም እሁድ ዕለት በአንድ ግለሰብ ላይ ጥቃት መድረሱን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ በጋምቤላ ከተማ በተለይም በሞተርና በባጃጅ በመቀሰቃስ በሰዎች ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ሐይሎች በነዋሪው ላይ ከፍተኛ ስጋት መፍጠራቸውን ጠቁመዋል፡፡

በጋምቤላ ከተማው ከአራት ቀን በፊት ምሽት 3 ሰዓት ገደማ አንድ ጤና ባለሙያ ማንነታቸው በውል ባልተገለጸ ሰዎች በደረበት ጥቃት ህይወቱ ማለፉን አስተያየታቸውን የሰጡን የከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በከተማው መሰል ጥቃቶች መበራከታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ ከሁሉት ሳምንት በፊት ሰኔ 1/2016 በከተማው በአንድ መዝናኛ ቦታ በነበሩ ሰዎች ላይ በተሸከርካሪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሐይሎች ባደረሱት ጥቃትም 9 ሰዎች ቆስሎ እንደነበር አብራርተዋል፡፡ በሰዎች ላይ የሚያደርሱ ጥቃት መበራከታቸውን ተከትሎ ረጅም ርቀት የምንቃሰቃሱ ተሽከርካሪዎች በተለይም ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን ያለ እጀባ መሄድ አዳጋች እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ ከክልሉ ዋና ከተማ ወደ ኑዌር ዞን የሚሄዱ የትራንስፖርት አገልግሎት ከተቋረጠ አንድ ሳምንት እንደሆነውም ስሜ አይገለጽ ያሉ የከተማ ነዋሪ ለዶቸቬለ ተናግረዋል፡፡በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ

በከተማው ጥቃት የሚያደርሱ ግለሰቦች የተደራጁ እና በመሳሪያ የታገዘ ጥቃት እንደሚያደርሱ ሌላው የከተማው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ በአንድ አንድ አካባቢዎች ማንነትን መሰረት ያደረገና አልፎ አልፎ ደግሞ በግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ጥቃቶች እንደሚያደርሱ ገልጸዋል፡፡ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሱ ግለሰቦችም ባለመያዛቸውና ለህግ ባለመቅረባቸው ጥቃቱ በተለያዩ ቦታ ላይ መበራከቱንና በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ እንደሚገኝ አክልለዋል፡፡

 በጋምቤላ ከተማ በተለይም በሞተርና በባጃጅ በመቀሰቃስ በሰዎች ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ሐይሎች በነዋሪው ላይ ከፍተኛ ስጋት መፍጠራቸውን ነዋሪዎች ጠቁመዋል
በጋምቤላ ከተማ በተለይም በሞተርና በባጃጅ በመቀሰቃስ በሰዎች ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ሐይሎች በነዋሪው ላይ ከፍተኛ ስጋት መፍጠራቸውን ነዋሪዎች ጠቁመዋልምስል Privat

በዚህ ሰኔ ወር መጀመሪያ በአንድ ሆቴል ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል ከተባሉ ግለሰቦች መካከል ሁለት ሰዎች ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ስለመዋላቸው አንድ ስማቸው እንዲሰጠቀስ ያልፈተለጉ የፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ተናግረዋል፡፡ በከተማ የሚደርሱ ጥቃቶች መበራከትም በህገ ወጥ መሳሪያ የታጠቁ ግለሰቦች በከተማው በመኖራቸው እንደሆነም አክለዋል፡፡የተፈናቃዮች ቅሬታ በጋምቤላ- ኢታንግ

በጋምቤላ ክልል ውስጥ በሰዎች ላይ በተደጋጋሚ ደርሷል የተባሉ ጥቃቶችና ግዲያዎችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲሰጡን ከጋምቤላ ክልል ፖሊሰ ኮሚሽን፣ ከክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ እንዲሁም ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ለቀናት ያደረግነው ሙከራ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በሲቪል ሰዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች መድረሳቸውንና በሰው እና ንብረት ላይ ከዚህ ቀደምም ጉዳቶች መድረሳቸውን የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ፀሀይ ጫኔ