በጄዳ የኢትዮጵያውያን ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ምሩቃን | ኢትዮጵያ | DW | 08.07.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በጄዳ የኢትዮጵያውያን ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ምሩቃን

በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤት የትምህርት ስርዓት እና ወግ እና ባህላቸውን አውቀው ያድጉ ዘንድ በውጭ ያሉ የኢትዮጵያውያን ያቋቋሟቸው ትምህርት ቤቶች የሚጫወቱት ሚና የጎላ ነው።

default

በሳውዲ ዐረቢያ እና በሌሎች የዐረብ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሁለት ዓመት ኮንትራት የተገደበ በመሆኑ በሀገሪቱ ምንም ያህል ቢቆዩም ዜግነት ማግኘትምም ሆነ ከአብራካቸው የሚወለዱትንም በሚኖሩባቸው ሀገሮች ዩኒቨርሲቲምና ኮሌጆች የማስተማር መብት የላቸውም። ይህ መሰራታዊ መብት የተነፈጋቸው እነዚሁ ኢትዮጵያውያን አጠቃላዩ ኑሮዋቸውና ስራቸው በሚያሰሩዋቸው ዐረባውያን ይሁንታ ላይ ጥገኛ በመሆኑ የሚገፉት ኑሮ አስተማማኝ አይደለም። ኢትዮጵያውያኑ ይህንን ችግር ለማቃለል በጄዳ ከአስራ አራት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ከፍተዋል። አንድ ሺህ አምስት መቶ ተማሪዎች ያሉት ይኸው ትምህርት ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፉት ሁለት ዓመታት የቅድመ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎችን ሰሞኑን አስመርቆዋል። ተማሪዎቹ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በቀትታ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመግባት ትምህርታቸውን ሊከታተሉ ይችላሉ።

ነቢዩ ሲራክ

አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች