በጄኔቭ የኢትዮጵያዉያን የተቃዉሞ ሰልፍ | ኢትዮጵያ | DW | 20.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በጄኔቭ የኢትዮጵያዉያን የተቃዉሞ ሰልፍ

ከተለያዩ የአዉሮጳ ሃገራት የተዉጣጡ ኢትዮጵያዉያን በዛሬዉ ዕለት ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።

በተለያዩ ሃገራት በስደት የተበተኑ ኢትዮጵያዉያን ስለሚገጥማቸዉ ችግር ለተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እንደሚያሳዉቁ የገለፁት የሰልፉ አስተባባሪዎች፤ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ፖለቲካ እና የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለማሳወቅ መሰብሰባቸዉንም አመልክተዋል። ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ መሆናቸዉን የገለፁልንን አቶ ዉሂብ የሺጥላን ስለሰልፉ ዓላማ እንዲያስረዱን በስልክ አነጋግረናቸዋል።

ሸዋዬ ለገሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic