በጄኔራል ሰዓረ መኮንን ላይ ጥቃት መድረሱ ተረጋገጠ | ኢትዮጵያ | DW | 22.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በጄኔራል ሰዓረ መኮንን ላይ ጥቃት መድረሱ ተረጋገጠ

ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ላይ ጥቃት መፈጸሙን ከዕኩለ ለሊት በኋላ በብሔራዊ ቴሌቭዥን ቀርበው አረጋገጡ።

ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ላይ ጥቃት መፈጸሙን አረጋገጡ። ጠቅላይ ምኒስትሩ ከዕኩለ ለሊት በኋላ በብሔራዊ ቴሌቭዥን ቀርበው በሰጡት መግለጫ በባሕር ዳር በተፈጸመው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ምኒስትሩ በጄኔራል ሰዓረ መኮንን ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከባሕር ዳሩ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገልጸዋል።  ጠቅላይ ምኒስትሩ «ይህ በአማራ ክልል ያጋጠመውን ችግር እና የመፈቅለ መንግሥት ሙከራ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ሆኖ እያስተባበረ እና እየመራ የነበረውን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በቅጥረኛ የተገዙ የቅርብ ሰዎች አሁን አመሻሽ ላይ የምንወደውን የምናከብረውን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም መሰል ጥቃት ተፈፅሞበታል» ብለዋል።

በጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል የተባሉ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ተናግረዋል።

እሸቴ በቀለ
ተስፋለም ወልደየስ