በጀርመን ጥቁር ፖለቲከኛና ዘረኝነት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 20.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

በጀርመን ጥቁር ፖለቲከኛና ዘረኝነት

ልጁ በጣም ጮክ ብሎ፥ “ ደንታዬ አይደለም፤ ለኔ አንድ ምጥማጥ ባሪያ ምጥማጥ ነው” አለ። ጠጋ አልኩና፤ ዝም ብዬ ብቻ ተመለከትኩት። ከዚያም ልጁ፥ አሁኑኑ ድምጥማጥህን እንዳላጠፋው” ሲል በድጋሚ ጮኸ።

ለዘረኝነት ቦታ የለም!

ለዘረኝነት ቦታ የለም!

ኢብራይሞ አልቤርቶ በትውልድ ሞዛንቢካዊ ሲሆን፤ ሽቬድት በተባለች የምስራቅ ጀርመን አነስተኛ ከተማ ውስጥ ዝነኛ ነው። ታዲያ በከተማው ዝነኝነቱ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ማለት የSPD ፓርቲ ጥቁር ተወካይ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ ቦክሰኛም በመሆኑ ነው። ኢብራይሞ ከሞዛምቢክ ወደ ቀድሞው የምስራቅ ጀርመን ሲመጣ በቦክሰኝነት ነበር። በርካታ የውጭ ሀገር ነዋሪዎች በከተማዋ የሚገኙ ቀኝ ፅንፈኞችን ፍራቻ አካባቢውን ለቀው ቢሸሹም፤ ኢብራይሞ ግን ዛሬም በዛች ከተማ ነዋሪ ነው።

ማንተጋፍቶት ስለሺ