በጀርመን የውጭ ዜጎች ጥላቻ መባባሱ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 20.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

በጀርመን የውጭ ዜጎች ጥላቻ መባባሱ

በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ጀርመን መግባታቸውን በመቃወም ፔጊዳ በጠራው በዚሁ ሰልፍ ላይ የጀርመን ባንዲራን ያየዙ ታዳሚዎች« ውጡ !ውጡ!» የሚሉ መፈክሮችን አስተጋብተዋል ።

በጀርመን ቀኝ ፅንፈኝነትና የውጭ ዜጎች ጥላቻ እየተሰፋፋ በመሄድ ላይ መሆኑ የሃገሪቱ ካቢኔ አስጠነቀቀ ።የጀርመን የፍትህ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ ሁኔታውን እጅግ አሳሳቢ ብለውታል ።የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቶማስ ደሚዜር ደግሞ ዜጎች ጥላቻን የሚቃወም አቋም ሊይዙ እንደሚገባ አሳስበዋል ።ማሳሰቢያዎቹ የተነገሩት ፀረ-እስልምና አቋም ያለው በምህፃሩ ፔጊዳ የተባለው ንቅናቄ ትናንት በምሥራቅ ጀርመንዋ በድሬ-ስደን ትልቅ የውጭ ዜጎች ጥላቻ የተንፀባረቀበት ሰላማዊ ሰልፍ ካካሄደ በኋላ ነው ። በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ጀርመን መግባታቸውን በመቃወም ፔጊዳ በጠራው በዚሁ ሰልፍ ላይ የጀርመን ባንዲራን ያየዙ ታዳሚዎች« ውጡ !ውጡ!» የሚሉ መፈክሮችን አስተጋብተዋል ።በትናንቱ ሰልፍ ላይ ከ15 እስከ 20 ሺህ የተገመቱ ሰዎች ተካፍለዋል ።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ