በጀርመን የእስራኤል ባንዲራ መቃጠሉ መወገዙ   | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 12.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

በጀርመን የእስራኤል ባንዲራ መቃጠሉ መወገዙ  

በተለያዩ የጀርመን ከተሞች በተካሄዱ ተቃዉሞዎች ፀረ ሴማዊ መፈክሮች መሰማታቸውን የጀርመን መንግሥት አውግዟል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:28

የእስራኤል ባንዲራ መቃጠሉ መወገዙ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማነት እውቅና መስጠታቸውን በመቃወም በርሊንን ጨምሮ በተለያዩ የጀርመን ከተሞች በተካሄዱ ተቃዉሞዎች ላይ ፀረ ሴማዊ መፈክሮች መሰማታቸውን የጀርመን መንግሥት አውግዟል። በነዚሁ ሰልፎች የእስራኤል ባንዲራ መቃጠሉንም አሳፋሪ ሲል ኮንኗል። የዶቼቬለ ዋና አዘጋጅ አኒስ ፖል ድርጊቱ ሀሳብን በነጻ ከመግለፅ እና ከዴሞክራሲ መብቶች ጋር የማይገናኝ ነው ስትል በጉዳዩ ላይ በጻፈችው ሀተታ ገልጻለች። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ያቀርበዋል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል 
ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች