በጀርመን አንድ የኒዎ ናዚዎች ቡድን ላይ የጀመረዉ ምርመራ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

በጀርመን አንድ የኒዎ ናዚዎች ቡድን ላይ የጀመረዉ ምርመራ

እ አ አ በ 2000 እና በ 2007 ዓም መካከል 10 ሰዎችን ገድሏል በተባለው በጀርመን በህቡዕ በሚንቀሳቀሰው የኒዎ ናዚዎች ቡድን አባል በሆነችው ቤአት ሼፐ እና በሌሎች አራት ተባባሪዎችዋ ላይ የተመሠረተውን ክስ ምርመራ ዛሪ በደቡባዊ ጀርመን በሙኒክ ላዕላይ ፍርድ ቤት ጀምሮአል።

የዛሪ ሁለት ዓመት መንገድ ዳር የሆነ ነገር ተቃጥሎ አመድ ለብሶ የታየዉ መለስተኛ አዉቶቡስ ዉስጥ ፖሊስ የሁለት ወጣቶች ሪሳ በማግኘቱ ነበር  ተጠርጣሪዎቹ፤  በድንገት የተገኙት እና የተያዙት ። ከጥቂት ሰአታት በፊት በዚያኑ ቀን በአካባቢዉ በሚገኝ አንድ ባንክ 70 ሺ ይሮ ሲዘረፍ  ሁለት የብስክሌት አሽከርካሪዎች እንደነበሩ የአይን ምስክሮች ገልጸዋል።

እጅግ አክራሪ የሆነው በህቡዕ ይንቀሳቀስ የነበረው የአፍላ ናዚዎች እንቅሥቃሴ፤ በተለያዩ ጊዜያት 9 ቱርካውያንናና አንድ ግሪካዊ እንዲሁም አንዲት ጀርመናዊት ፖሊስ መግደሉ ታውቋል።

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረበችው ዋና ተከሳሽ፤ ፤ የዚህ ሁሉ ግድያ ዋና ግብረ- አበር ተብላ የተጠረጠረችው  ቤአተ ቼፐ የተባለችው ናት። ዑቨ ሙንድሎስና ዑቨ Böhnhardt  የተባሉት የዚህ የህቡዕ ድርጅት መሥራቾች፤ እንደተነቃባቸው ህይወታቸውን  በራሳቸው እጅ ማጥፋታቸው ነው የተነገረው። ዋናው ጥያቄ እነዚህ ወገኖች የመንግሥት ፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ሳያውቁባቸው እንዴት 10 ዓመት ሙሉ  አቅድ እያወጡ የሰው ነፍስ አጠፉ ? የሚለው ነው። የፍርዱ ምርመራና ሂደት  ሰፊ ዓለም አቀፍ ትኩረት አግኝቷል ፣ በተለይ በቱርክ!በዛ ያሉ የቱርክ የህዝብ እንደራሴዎች   ም/ቤት አባላትም ፣ የምርመራውን ሂደት ለመከታተል ወደ ሙዑሸን ተጉዘዋል። ዝርዝሩን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሃይለሚካኤል አጠናቅሮታል።

ይልማ ሃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic