በድንበር ውዝግብ 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለዋል | ኢትዮጵያ | DW | 07.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በድንበር ውዝግብ 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለዋል

የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች የድንበር ውዝግብ የተፈናቀሉ 1.1 ሚሊዮን ገደማ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ጥረት ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ የመረጃ ቋት (ReliefWeb) ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም ከ46 ሚሊዮን ዶላር በላይ መመደቡን አስታውቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:19

1 ሚሊዮን ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል

ከኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ የድንበር አካባቢዎች የተፈናቀሉ 584,000 ዜጎች ወደ ቀደመ መንደራቸው መመለስ ቅድሚያ ተሰጥቶታል። ቀሪዎቹ ተፈናቃዮች በሌሎች አካባቢዎች የሚሰፍሩ ይሆናል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ በ12 ከተሞች 86,000 ተፈናቃዮችን ለማስፈር ጥረት በማድረግ ላይ ነው። በተመረጡ 12 ከተሞች 12,000 የመኖሪያ ቤቶች በመገንባት ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት በድንበር ውዝግቡ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የሚገኙባቸውን ቆሎጂ 1 እና ቆሎጂ 2 የተባሉ መጠለያዎች ለመዝጋት መወሰኑንም አስታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የድንበር ውዝግብ ከአንድ ሚሊዮን በላይ መፈናቀላቸውን ቀደም ብሎ መግለፁ አይዘነጋም። 
መክብብ ሸዋ
እሸቴ በቀለ  

Audios and videos on the topic