1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በድሬደዋ ከኹከት ጋር የተያዙ እየተለቀቁ ነዉ 

ሰኞ፣ የካቲት 4 2011

የድሬደዋ አስተዳደር በቅርቡ በከተማው በተካሄደው ተቃውሞ እና ሁከት ጋር በተያያዘ ጠረጠርኳቸው በሚል በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ከሦስት መቶ በላይ ሰዎች የአብዛኞቹን ክስ በማቋረጥ በነፃ እየለቀቀ ይገኛል። የአስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር ኮማንደር አለሙ መርጋ ተጠርጣሪዎቹ ስለተለቀቁበት ምክንያት አስረድተዋል ፡፡

https://p.dw.com/p/3D9i7
Äthiopien Dire Dawa City
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

ተጠርጣሪዎቹ ክሳቸው ተቋርጦ ተፈተዋል

 

የድሬደዋ አስተዳደር በቅርቡ በከተማው በተካሄደው ተቃውሞ እና ሁከት ጋር በተያያዘ ጠረጠርኳቸው በሚል በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ከሦስት መቶ በላይ ሰዎች የአብዛኞቹን ክስ በማቋረጥ በነፃ እየለቀቀ ይገኛል ። ከቀናት አስር በኃላ በቂ ማስረጃ ባለመኖሩ የተለቀቁ ተጠርጣሪዎችና ቤተሰቦች እንዲሁም ወዳጆች  በእምባ ተራጭተዋል ፡፡ በከተማው ለቀናት የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የፀጥታ ሀይሉ በወሰደው ሰፊ እርምጃ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎችን አፍሶ በመያዝ ከአስራ አምስት ቀናት በላይ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው ሲመረመር ቆይቷል ፡፡ ከነዚህ ተጠርጣሪዎች ሁለት መቶ አስራ ስምንት የሚሆኑትን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና ፖሊስ ውሰኔ ክሳቸው ተቋርጦ በነፃ እንዲለቀቁ ተደርጓል፡፡

ከሳምንት በፊት በሀላፊነት የተሾሙት የአስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር ኮማንደር አለሙ መርጋ ተጠርጣሪዎቹ ስለተለቀቁበት ምክንያት አስረድተዋል ፡፡ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ተጠርጣሪዎችን በመልቀቅ ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ከመልቀቃቸው በፊት ከተጠርጣሪዎች ፣ ከቤተሰብና በነፃ ጥብቅና ቆመው ከነበሩ የህግ ባለሞያዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ኮምሽነሩ ስለውይይቱ ዓላማ ተናግረዋል ፡፡ በተለያዩ ቀናት በተካሄደው በዚህ ውይይት በከተማው የተፈጠረውን ሁከት ተከትሎ በጅምላ ተይዘው የቆዩ ተጠርጣሪዎች ከድርጊቱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖር ጭምር መሆኑነንና ፣ በምርመራ ሂደትም ከመርማሪዎች ከብቃት ጋር የተያያዙ ችግሮች እንደነበሩ ተነስተዋል ፡፡ ወጣቹም በሰላማዊ መንገድ ትግላችንን እንቐጥላለል ብለዋል ፡፡ከህብረተሰቡ ለተነሱት ጉዳዮች በፖሊስ እና ዐቃቤ ህግ በኩል ተወስደው የሚታረሙ መሆኑ ተገልፇል፡፡በሌላ በኩል ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ፍ/ቤት ቀርበው ግዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ከነበሩና ዛሬ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ ዘጠና ተጠርጣሪዎች አብዛኞቹን ክስ በማቋረጥ መልቀቃቸው ለፍ/ቤቱ ተገልፃል፡፡


መሳይ ተክሉ 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ