በድሪደዋ የተቀሰቀሰዉ አዲስ ግጭት
ማክሰኞ፣ ጥር 14 2011ማስታወቂያ
በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከከትናንት አመሻሽ ጀምሮ ልዩ መጠርያው ፖሊስ መሬት በሚባለው አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተነገረ ፡፡ ግጭቱ ዛሬም ባለመብረዱ የአስተዳደሩ ፖሊስ ፣ የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሀይል ግጭቱን ለማብረድ እርምጃ ሲወስዱ መዋላቸዉ ከቦታዉ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። ግጭቱን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ቁጣ የተለያዩ ወጣቶች ችግሩ ወደተፈጠረበት አካባቢ በመንቀሳቀሳቸው ሁኔታው ተባብሶ እነደነበር ተገልፆአል።
መሳይ ተክሉ
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ