በዳርፉር ውዝግብ ሳቢያ የምትወቀሰው ሱዳንና የጀርመን የኢንዱስትሪ ኩባንያዎች፧ | ኤኮኖሚ | DW | 20.03.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

በዳርፉር ውዝግብ ሳቢያ የምትወቀሰው ሱዳንና የጀርመን የኢንዱስትሪ ኩባንያዎች፧

ከጀርመን የልማት ተረድዖ ሚንስቴር ጋር በመጣመር፧ አንዳንድ የጀርመን ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ተጠሪዎች፧ ሰሜንና ደቡብ ሱዳንን ጎብኝተው ተመልሰዋል። ከጉብኝቱ በፊት፧ የጀርመን የአረንጓዴው ፓርቲ፧ ብርቱ ተቃውሞ ያሰማ ሲሆን፧ ጉዱንም ለፓርላማ በማቅረቡ፧ ከነገ በስቲያ ክርክር ይደረግበታል።

የ.ተ.መ.ድ፧ልዊስ ሞሬኖ ኦካምፖ፧ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዳርፉር፧ ግፍ ሳይፈጽሙ እንዳልቀሩ የጠረጠሯቸውን ሱዳናውያን ባለሥልጣናት ሥም ጠቅሰዋል።

የ.ተ.መ.ድ፧ልዊስ ሞሬኖ ኦካምፖ፧ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዳርፉር፧ ግፍ ሳይፈጽሙ እንዳልቀሩ የጠረጠሯቸውን ሱዳናውያን ባለሥልጣናት ሥም ጠቅሰዋል።

ወደ ሱዳን ተጎዞ ከነበረው የልዑካን ቡድን አባላት መከከል፧ Cramm & Co. Hamburg የተሰኘውን የኢንዱስትሪ ኩባንያ ተጠሪ Philipp Müller ን የዶቸ ቨለዋ Stefanie Duckstein አነጋግራቸዋለች ተክሌ የኋላ አቀናብሮታል።
ፊሊፕ ሙዑለር የኢንዱስትሪ ኩባንያቸው በውጭ ንግድ ላይ ያተከረ፧ ሱዳን ውስጥም የንግድ እንቅሥቃሴውን ሲያካሂድ 50 ዓመታት ያስቆጠረ መሆኑን እንደመግለጻቸው መጠን፧ ለሱዳን እጅግ ተፈላጊዎቹ የኢንዱስትሪ ምርቶች የትኞቹ እንደሆኑ ተጠይቀው ነበር።
«በአመዛኙ የሚፈለጉት ማሺኖች ናቸው። መለዋወጫ መሣሪያዎች፧ የግንባታ መሣሪያዎች፧ መሬት ቆፋሪ፧ አፈርና ድንጋይ ዛቂ ማሺን፧ የስሚንቶ ቱቦዎች...ሁሉም የሚፈለጉት፧ ከዚህ ከግንባታ ዘርፍ ጋር የተያያዙ ናቸው«
Herr Müller ከሁለት ሳምንት በፊት በዚያ ያደረጉት የእርሳቸውና የልዑካኑ ቡድን አባላት ጉብኝት ዋና ዓላማም ሆነ አጀንዳ ምን እንደነበረ ሲያብራሩ....
«የጉብኝታችን ዋና ዓላማ፧ የፌደራሉ መንግሥት፧ የኤኮኖሚ ሚንስቴር ልዑካን ቡድን ጉዞ ዋና ዓላማ፧ በሰሜን ሱዳንም ሆነ በደቡብ ሱዳን፧ በኤኮኖሚ ትብብር የቱን ያህል ተባብሮ መሥራት እንደሚቻል ለማጥናት ነው። እናም በጥናታችን መሠረት፧ ሰሜኑ ሱዳን፧ በልማት፧ ከሞላ ጎደል የገሠገሠ፧ ደቡቡ ግን፧ በረጅም ጊዜው ጦርነት ሳቢያ፧ ገና ብዙ እንደሚቀረው ለመገንዘብ በቅተናል«
ሄር ሙዑለር፧ ስለአሁኑ የሱዳን ይዞታ ሲያብራሩ፧
የሰሜኑ ሱዳን ይዞታ በግንባታ ረገድ ከደቡቡ እጅግ የተሻለ መሆኑን ደቡቡ በመሠረተ-ልማት የመዋቅር ጉድለት እንደሚታይበት የግሉ የኤኮኖሚ ዘርፍም እንደታጎለ መሆኑን ነው ያብራሩት። ያም ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሁኔታዎችን ለማስተካከል ሥርዓት ለማስያዝ በመሞከር ላይ መሆኑን ነው ያስረዱት። የመሠረተ-ልማቱ አቅድ በአግባቡ አልወጣም። አስተማማኝ ጎዳናዎች አልተሠሩም።ባንክም የለም። ዕቃ የሚያጓጉዙ ከኬንየሚገቡ ጸጭነት ተሽከርካሪዎች ናቸው። ደቡብ ሱዳን ውስጥ ብዙ መሠራት እንዳለበት ነው ጎብኚው በበኩላቸው ያስገነዘቡት። የሱዳን ማዕከላዊ መንግሥት፧ በዳርፉር የሚካሄደውን የህዝብ ጭፍጨፋ እንዲገታ እርምጃ ባለመውሰዱ፧ ዘወትር እንደተወቀሰ ነው። የልዑካኑ ቡድን፧ ለመሆኑ፧ በዚህ ርእሰ-ጉዳይ ላይ ተነጋግሮ ነበር ወይ?
« ይህን ርእስ፧ ከይፋው ጉዳያችን ውጭ ተነጋግረንበታል። ግን በዝርዝር አይደለም የተወያየንበት። መንግሥት ራሱ፧ በዚህ ጉዳይ ላይ በፍጹም የመወያየት ፍላጎት አላሳየም። የልዑካኑ ቡድን አባላትም፧ የፖለቲካ ጉዳዮችን እንዲያነሱ ኀላሲነት የተሰጣቸው አልነበሩም።«
ከልዑካኑ ጉዞ በፊት የአረንጓዴው ፓርቲ፧ የዳርፉር ውዝግብ ይበልጥ በተባባሰበት በአሁኑ ወቅት፧ የኤኮኖሚ ትብብር ማድረግ አስፈላጊ አይደለም ሲል ነቀፌታ ሰንዝሯል። ኩባንያችሁ ለእንዲህ ዓይነቱ ነቀፌታ፧ ምንድን ነው መልሱ?ለሚለው ጥያቄ፧ ፊሊፕ ሙዑለር፧....
«እንዲህ ዓይነቱ ጥያቄ፧ በእርግጥ ከንግድ ጋር የተያያዘ ነው። ገጠሩን ሱዳን፧ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር የሚያስተሣሥር ሲሆን፧ ለአገሪቱ የኤኮኖሚ ግንባታም፧ እጅጉን ተፋላጊ ነው። እናም ይህን የአረንጓዴውን ፓርቲ ጥያቄ አግባብነት ያለው ሆኖ አላየውም።«
በንግድ ሥምሪት፧ ማዕከላዊው መንግሥት ቀንበሩ እንዲቃለልለት ማድረግ ይሆናል ቢባልም፧ እንሁ የኢንዱስትሪ ተጠሪ፧ ግለሰብንና የግል የንግድ ልውውጥን የመንግሥት እንደሆነ አድርገጎ በኀላፊነት መጠየቅ አይቻልም ባይ ናቸው። የሲቭል አገልግሎት የሚሰጡ የአገሩን ህዝብ የሚጠቅሙ እንደ መድኀኒት፧ የመሳሰሉትን ኩባንያቸው እንደሚያቀርብና ይህ በቀጥታ ከመንግሥት ፖለቲካ ጋር የሚያገናኝ ሊሆን አይገባም የሚል መከራከሪያ ሐሳብ ሠንዝረዋል። እንደ «ዚመንስ« ኩባንያ የእርሳቸውም፧ ተመሳሳይ ተግባር በመፈጸም፧ በሱዳን ያካሂድ የነበረውን የሚያካሂደውን፧ ንግድ አቋርጦ ለመውጣት ተመሳሳይ ድርጊት ይፈጽም እንደሁ ተጠይቀውም፧..
«እንደተገነዘብኩት፧ የዚመንስ ኩባንያ፧ ከሱዳን የሚወጣው፧ የአሜሪካ መንግሥት በጠም ጠንካራ ተጽእኖ በማሳረፉ ነው። ተመሳሳይ አዝማሚያ በባንክ ረገድ ማጋጠሙን ልብ ብለናል። ያም ሆኖ General Electric Motors ዚመንስ ኩባንያ ከሱዳን ከወጣ በኋላ፧ ለሱዳን በሰፊው የተጠየቀውን ላማቅረብ መዘጋጀቱ የሚገርም ነው