በዳርፉር ሰላም አስከባሪ ሃይል ላይ የተጣለ ጥቃት | አፍሪቃ | DW | 15.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

በዳርፉር ሰላም አስከባሪ ሃይል ላይ የተጣለ ጥቃት

ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በዳርፉር ፣ ሱዳን ፣ ሰባት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች መገደላቸዉና ወደ አስራ ሰባት የሚሆኑ ወታደሮች ደግሞ በጠና መቁሰላቸዉ ተነግሮአል። ወታደሮቹ በሙሉ የታንዛያ ተወላጆች እንደሆኑም ታዉቆአል።

በምዕራባዊው ሱዳን ክፍለ ሀገር፣ በዳርፉር፣ ይህ የሰላም አስከባሪ ጓድ ተልእኮዉን ከጀመረ፤ ከአምስት ዓመት ወዲህ ከባድ ጥቃት ሲደርስበት የመጀመርያዉ መሆኑም ተነግሮአል፤የ UNAMID ማለት የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪቃ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ዉዝግብ ባልተለየዉ የምዕራብ ሱዳን ግዛት ዳርፉር ዉስጥ የተገደሉት ባሳለፍነዉ ቅዳሜ ነበር። ደቡባዊ ዳርፉር ግዛት ኮር አቤቼ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘዉ የጦር ሰፈር የተገደሉት የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪቃ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ጓዶች የታንዛንያ ተወላጆች እንደሆኑ ተነግሮአል። የታንዛንያ የግድያዉን ሁኔታ ለማጣራት አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አካባቢዉ ላይ መላክዋን የጦር ሃይል ቃል አቀባይ ኮነሪል ካፓባላ ምጋዪ ዛሪ ለዶቸ ቬለ ግልጸዋል፤ የተመ በስፍራዉ ላይ ተጨማሪ የጸጥታ ሰራዊት ማሰማራት እንዳለበት የጠቀሱት የታንዛንያዉ የጦር ሃይል ቃል አቀባይ፤

«የጸጥታ ሃይላቱ የተገደሉበትን ሁናቴ ለማጣራት ልዑካንን ከመላክ ባሻገር በቦታዉ ከመላክ ባሻገር፤ በስፍራዉ ያሉት የፀጥታዉ ሃይላት እንዲህ አይነት አጋጣሚ ላይ ሲወድቁ መቋቋም እንዲያስችላቸዉ የጦር ሃይሉን እንዲጠናከር የተመድ የወታደሩ ቁጥር እንዲጨምር መጠየቅ የሚያስፈልግ ይመስለናል። በሌላ በኩል እንደሚታወቀዉ፤ በቦታዉ ላይ ለጥበቃ የምንጠቀምበት መሳርያ ቀላል አይነት ብቻ ነዉ ምክንያቱም እንዲህ አይነት ሁኔታ ይገጥመናል ብለን አላሰብንም» ባለፈዉ ቅዳሜ በዳርፉር ለደረሰዉ ጥቃት እስካሁን ሃላፊነትን የወሰደ ወገን የለም። በአካባቢዉ ላይ የሚንቀሳቀሰዉ የሱዳን ነጻ አዉጭ ጦር የተሰኘ የዓማጺያን ቡድን በበኩሉ ጥቃቱን ያደረሰዉ ከመንግስት ጋር ሽርክና ያለዉ ሚሊሽያ መሆኑን ማመልከቱ ተዘግቦአል። ይህ ጥቃት በዳርፉር ሰፍሮ ለሚገኘዉ ጦር ምን መልክትን ያስተላልፍ ይሆን በአፍሪቃ ሕብረት ጉዳዮች ላይ ላይ ጥናት የሚካሂዱት ዶክተር መሃሪ ታደለ እንደሚሉት፤ የሰላም ማስከበሩን ተግባር ተግባራዊ ማድረግ አልቻለም።

የታንዛንያ የጦር ሃይል ቃል አቀባይ ኮነሪል ምጋዪ፤በዳርፉር በተመ ሰላም አስከባሪ ስር በሚገኘዉ በታንዛንያ የጦር ሰራዊት ላይ በደረሰዉ አደጋ ምክንያት አገራቸዉ በዳርፉር ያላትን የጦር እንደማታሶጣም ተናግረዋል፤ ከዚህ ጥቃት በኋላ ለዓመታት ዉዝግብ ባላጣት ዳርፉር የአፍሪቃ ሕብረት ሀገራት ወታደሮቻቸዉን ለመላክ ዉሳኔ ላይ ይደርሱ ይሆን፤ በአፍሪቃ ሕብረት ጉዳዮች አዋቂዉ ዶክተር መሃሪ ታደለ እንደሚሉት፤ እንብዛም ለዉጥ አያመጣም ባይ ናቸዉ።

በሱዳን ዳርፉር የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪቃ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ተልዕኮዉን ከጀመረ ይህ ጥቃት ሲደርስ ከአምስት ዓመት ወዲህ ከባዱ መሆኑ ነው። በዳርፉር ሰፍረው የሚገኙት የ UNAMID ሰላም አስከባሪ ወታደሮችና ፖሊሶች ቁጥር 19,700 ግድም እንደሆነ ተገልጾአል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic