በደቡብ ሱዳን ውዝግብ ላይ የመከረው የኢጋድ ስብሰባ | አፍሪቃ | DW | 18.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

በደቡብ ሱዳን ውዝግብ ላይ የመከረው የኢጋድ ስብሰባ

ደቡብ ሱዳን ውዝግብ የቀጠለባትን የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖችን እንደገና ወደ ድርድሩ ጠረጴዛ የማምጣት ዓላማ ይዞ የተነሳ  አዲስ የውይይት ዙር ዛሬ በአዲስ አበባ የአፍሪቃ ህብረት አዳራሽ ተጀመረ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:17

እልባት የጠፋለት የደቡብ ሱዳን ቀውስ

በተቀናቃኞቹ ወገኖች መካከል በጎርጎሪዮሳዊው 2015 ዓም ተደርሶ የነበረው  የሰላም ስምምነት ባለፈው ዓመት ከከሸፈ ወዲህ የሀገሪቱ ህዝብ ስቃይና መከራ እየባሰ ሄዷል። ለዚህም የፖለቲካ መሪዎች ተጠያቂዎች ናቸው በማለት በስብሰባው ንግግር ያሰሙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወቅሰዋል።  የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ፣ በምህጻሩ ኢጋድ በጠራው በዚሁ ጉባዔ ላይ የአፍሪቃ ህብረት አባል መንግሥታት፣ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ እንዲሁም፣ ከሁሉም የኑሮ ዘርፎች የተውጣጡ ደቡብ ሱዳናውያን ተሳታፊዎች ሆነዋል።  

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic