በይቅርታው ላይ የተነሳው ተቃውሞ | ኢትዮጵያ | DW | 30.12.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በይቅርታው ላይ የተነሳው ተቃውሞ

በደርግ ዘመን የተገደሉት የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ መንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች ፣ ተፈርዶባቸው የታሰሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት ይቅርታ ጠይቀው እንዲፈቱ የሃይማኖት አባቶች የጀመሩትን ሽምግልና ተቃውመዋል ።

default

ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ እነዚህን የሟቾቹን ቤተሰቦች ቀጠሮ ይዘዋል ። የደርግ ግድያ የተጀመረባቸውን የ68 ባለሥልጣናት ቤተሰቦች ተወካይ አቶ አሸናፊ ሽፈራውን ከንግግሩ በፊት በስልክ አነጋግሬያቸው ነበር ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሸ መሐመድ