በዝግ የቀጠለዉ የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ | ኢትዮጵያ | DW | 23.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በዝግ የቀጠለዉ የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢህአዴግ በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ቀናት አንስቶ በዝግ ስብሰባዉን እያካሄደ ይገኛል። ከምክር ቤቱ ስብሰባ የሚወጣ አንዳችም መረጃ ባለመኖሩ ጉዳዩን በትኩረት የሚከታተለዉ ወገን የየራሱን ግምትና አስተያየት እየተዋወጠ ነው።

 በዋናነት የፓርቲዉን ሊቀመንበር ብሎም የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ይሰይማል ተብሎ የሚጠበቀዉ የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ለትናንት አንዳች ዉጤት ላይ ደርሳል ተብሎ ቢጠበቅም ያለምንም ፍንጭ ዛሬም ስብሰባዉ ቀጥሏል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ አንድ የፖለቲካ ተንታኞች ግን ሃሳብን ከላይ ወደታች ማዉረድ በለመደዉ በግንባሩ አካሄድ አዲስ ነገር እንዳልሆነ ይናገራሉ። ከአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ተከታዩን ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች