በዚምባብዌ፤ አዲሱ የፕረስ ሕግ ከወረቅት አላለፈም | ዓለም | DW | 03.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

በዚምባብዌ፤ አዲሱ የፕረስ ሕግ ከወረቅት አላለፈም

አሥራ ሁለት ዓመት በሙሉ በተከታታይ በጋዜኛነት በአሳለፍኩት የሕይወት ዘመኔ ውስጥ አንድ የተገነዘብኩት ጉዳይ ቢኖር የፕሬስ ነፃነት አለ ተብሎ በዚህ አገር በየጊዜው የሚዘከርለት ነገር ምንም መያዣ እና መጨበጫ የሌለው ሐሰት ነገር ነው።

ሌላው ቀርቶ በሕገ-መንግሥቱም ላይ ቢሆን ይህ በሌላው ዓለም የማንም ሰው መሠረታዊ ነፃነትና ሐሳብን የመግለጽ መብት በሕግ ታውቆ በአገራችን የተደነገገ መብት አይደለም። ማለት የምችለው ነገር ቢኖር የጋዜጠኛነት ሕይወቴ በመንግሥት ባዶ ፍሬ ከርሲክ መብትና ግዳጅ ላይ የተመሠረተ እንጂ ሌላ ምንም አዲስ ነገር የለውም። ልንገራችሁ ? ጋዜጠኛነት እና የጋዜጠኛ ሙያ በዝምባቡዌ አደገኛ እና ነርቭን የሚበጥስ ነው አንድን ሰውም አደጋ ላይ የሚጥል የሚከት ሙያ ነው።

እነዚህ ሁሉ ተደራርበውብኝ ነገሩን ቀጭ ብዬ ስመለከተው ጋዜጠኛ መሆኔ ትርፉ ምንድነው የሚለውን ጥያቄ በአእምሮዬ አንስቼ እራሴን እንድጠይቅ ያደርገኛል ወይም ደግሞ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቼ ሌላ ነገርስ ብጀምር አይሻልም ወይ የሚለውንም ጥያቄ እንዳነሳ ይገፋፋኛል።

የፕሬስ ሥራ አደገኛ ነው- በፕሬስ ዓለም ውስጥ ገብቶ መሥራት ትርፉ ለክትትልና ለበደል፣ ለግፍም ኢላማ መሆንና መጋለጥ ነው። በዚምባቡዌ የፕሬስ ነፃነት በገደብ ተለክቶ የተሰጠ መብት ነው። በአለፉት ዓመታት በተከታታይ ፈላጭ ቆራጩ ገዢው መንግሥት ለይስሙላ የፕሬሱን ዓለም ከቁጥጥርና ከተጣለበት ልግዋም ቀስ እያልን ነፃ አድርገን እንዲሰራና እንዲንቀሳቀስ እናደርገዋለን የሚለው ቃል መግባት እስከ አሁን ድረስ ሥራ ላይ ውሎ ይህ ነው የሚባል በዓይን የሚታይ ተጨባጭ ነገር ይዞልን ብቅ አላለም።

አሁንም ቢሆን ጋዜጠኞችን ፊት ለፊት የሚያሳድድና የሚያስፈራራ እነሱንም የሚቆጣጠር ሕግ በአገሪቱ አለ። በተለይ በዕለታዊ ጋዜጣና መፅሔት፣ በእነሱም ሕትመትና ዝግጅት ላይ የተሠማሩ ጋዜጠኞች ለዚሁ የመንግሥት ሕግ ወጥ እርምጃ የተጋለጡ ናቸው። አንድ ጋዜጠኛ ሥራውን ለማካሄድና ለመወጣት በየዓመቱ የሥራ ፈቃዱን መንግሥት ፈት ቀርቦ በገዛ አገሩ የግድ ማሳደስ አለበት የሚል ሕግ ተጥሎበታል።

የፕረስ ነፃነት ያለገደብ

የፕረስ ነፃነት ያለገደብእንግዲህ ይህን ፈቃድ ያልያዘ ወይም ያላራዘመ ጋዜጠኛ አንድ ነገር ጽፎ ቢገኝ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ እሰከ ሁለት ዓመት ድረስ እሥር ቤት ሊወረወር ይችላል። አንዳንዴ ደግሞ ለዚህ ደግሞ በቂ ማሥረጃዎች አሉን። ጋዜጠኛች ሕጋዊ የሥራ ፈቃዳቸውን እያሳዩም ወከባና ስድብ ዱላና ጥፊም ዛቻና ማስፈራራትም ይደርስባቸዋል።

በተለይ የአገሪቱ የዝምባቦዌ «የሕግ አስከባሪ» የሚባሉ ሰዎች እንደ ዕብድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ፎቶግራፍ አንሺዎችን ሲያዩ ነው። መንገድ ላይ ካሜራን ብድግ አድርጎ ፎቶ- ግራፍ ማንሳት ለአንድ ሰው ሕይወት አደገኛ ነው።

በአለፈው መስከረም ወር 2014 ዓ.ም. እ.አ.አ. አንድ የትራፊክ ፖሊስ ይዞኝ ቀጥቅጦ ለቀቀኝ፣ ጥፋቴ ፎቶግራፍ ማንሳቴ ነበር። ያነሳሁት ፎቶ ደግሞ ሌላ ነገር ሳይሆን ፖሊሶች እራሳቸው አንድ የከተማ ማመላለሻ አውቶብስ አቁመው ከእሱ ጋር ግግብ ይዘው ሲነታረኩ የሚያሳይ ነበር።

እሱን ጥለው እኔ ላይ ተረባረቡብኝ፣ የሥራ ፈቃዴን-ጋዜጠኛ ነኝ እያልኩ እያሳየሁአቸው በዱላቸው እየተፈራረቁ ወረዱብኝ። ማንም እንደሚያዉቅው እና እኔም እንደምረዳው የፕሬስ ነፃነትን ፣የተለያዩ ሓሳቦችና የተለያዩ አመለካከቶችን በአንደኛ ደረጃ ማስከበር ያለበት እና ማስተናገድ ያለበት መንግሥት ነው። የእኛንም የጋዜጠኞችን ደህንነትና ሥራችን እንዳይስተገጎል መንከባከብና ማስጠበቅ ኃላፊነቱ የእሱ የመንግሥት ፋንታ መሆን ነበረበት።

በመጋቢት ወር 2013 እ.አ.አ. አዲሱን ሕገ-መንግሥት የጋዜጠኛችን የፕሬስ ነጻነት የሚያውቀውና የሚያከብረውን አንቀጽ በትልቅ ጭብጨባና ደስታ ሁላችም ተቀብለን እፎይ ብለን ነበር። ግን ምን ይደረጋል በተጨበጭ በሥራ ተተርጎሞ ሲያዩት ሕጉ ባዶ ነው።

በዚህ አሁን በያዝነው በመጋቢት ወር 2015 የኢኮኖሚ ጥያቄዎችንና አርዕስቶችን የሚያስተናግደውን አንድ ጋዜጣ ቢሮ አንድ የቤት ዕቃ ቁሳቁሶችን የሚሸጥ ድርጅት በፖሊሶች ታጅቦ «አሳሳቢ» ባለዉ ምክንያት በርብሮ እና አመሰቃቅሎ ለመሄድ ችሏል።

የድርጅቱ የድርጅቱ ተወካይ እንደሚሉት አንድ ወደ ውጭ ውጥቶ ሰው ማንበብ የሌለበት እነሱ «ምሥጢራዊ » ያሉትን መረጃ ለማገድ እንደሆነ ለወሰዱት እርምጃቸው ምክንያት ሰጥተዋል። ይባስ ብለውም መረጃዎቹን በጋዜጠኛቹ › ተሰረቅን › ባይ ከሳሾች ሁነዋል።

ይህን ሁሉ ሲያደርጉ እነሱን የሚቆጣጠርና ተው ብሎ የሚከለክል የመንግሥት ክፍል አለመኖሩን ልብ ይሏል። ማለት የሚቻል አንድ ነገር ቢኖር ይህ ሕገ-ወጥ ሥራ በተለይ ፕሬሱን በተመለከተ ከመንግሥት አልፎ በንግድ ላይ የተሠማሩትም ቱጃሮች ጠግበውና በማን አለህብኝነት የጋዜጠኞችን እና የጸሓፊዎችን መብት እስከመግፈፍና መዳፈር ድረስ መሄዳቸውን ነው ።የጥፋት መጨረሻው ደግሞ ተስፋ የሚባለውም ነገር ድርግም ብሎ ሲጠፋ ነው።

የፕረስ ነፃነት ያለገደብ

የፕረስ ነፃነት ያለገደብአሁንማ ይባስ ተብሎ ለድህንነታችንና ለሕይወታችን የሚያሰጋ ሁኔታ ውስጥ ገብተናል። ጋዜጠኞች ተጠልፈው ይታገሉ፤ አለጥፋትና አለማስረጃ ያለክስ እሥር ቤት ይወረወራሉ። በመጋቢት 9 2015 እ.አ.አ. እነማን እንደሆኑ በአልታወቁ ሰዎች ጋዜጠኛው ኢታይ ዛማራ ተጠልፎ ተወስዶአል። ይህ ጋዜጠኛ ሞቶ ይሁን ወይም በሕይወቱ እንደአለ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም።

ጋዜጠኛው ዛማራ የፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤን መንግሥት ከሚተቹት ሰዎች መካከል አንደኛው ነው።ይህ በሙያ ባልደረባችን ላይ የደረሰው ያልታሰበ ሰለባ እኛን ያአገሪቱን ጋዜጠኞች በሙሉ እንደለ አስደንግጦናአል፣ይባስ ብሎም ይህ ሁኔታ የመናገርና የመጻፍ፣ አስተያየት እና ትችት የመሰንዘር መብታችንን እንደለ ተወርውሮ አሁን መሬት ላይ ተጥሎአል። ነግ በእኔ የሚል ፍረሃቻም በመካከላችን ነግሷል።

ሌላው አገሪቱ ዚምባቡዌ የገባችበትና የተዘፈቀችብት የኢኮኖሚና የፊናንስ ቀውስ እኛንም የሚዲያ ሰዎች ይኸው ችግር ደህና አድረጎ እንደ ሌላው የሕብረተሰቡ ክፍል ገርፎን አልፎአል። ብዙ ጋዜጣ አታሚዎች በቀውስ ሳቢያ ከስረው ቢሮአቸውን ለመዝጋት ተገደዋል። እኔ እራሴ ለአንደኛው የኦንላይን ጋዜጣ ዘጋቢ ሁኜ ስሠራ ከሰነበትኩ በሁዋላ ከመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም እ.አ.አ. ጀምሮ ደመወዜን አዘጋጁ መክፈል ስለአልቻለና ገቢም ስለሌው ከነአካቴው ቢሮውን ዘግቶ ሄዷል። በዚህ ከባድ የመከራ ዘመን ከአንድ መሥሪያ ቤት ብቻ በጽሑፍ ሥራ ላይ አንድ ጋዜጠኛ ተሰማርቶ ቤተሰቦቹንና ሚስቱን ልጆችን ጭምር መቀለብ፣ ማስተዳደር ቀላል ነገር እንዳልሆነ ማንም ሰው ሊገነዘብ ይችላል።

የፕረስ ነፃነት ያለገደብ

የፕረስ ነፃነት ያለገደብ

አንድ የቀረችኝ ትንሽ ተስፋ ቢትኖር፣ ይህ ሁሉ የመከራ ዘመን አንድ ቀን አልፎ እኛ ጋዜጠኞች ነፃ ሆነን የፕሬስ ነፃነቱንም ተቀዳጅተን አላንዳች ቁጥጥርና ፍረሃት ለአገራችን ዕድገትና ብልፅግና፣ ለሕዝቡም ድህንነትና መልካም ኑሮ፣ ለእናት አገራችንም ሕልውና የተለያዩ፣ የሚጻረሩና የሚፎካከሩ አስተሳሰቦችን አንስተን በመልክ በመልኩ እያፈረጥን እነሱን የምናስተናግድበት ጊዜ አይቀርም፣ ይመጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ እሱንም እጠብቃለሁ።

የ36 አመቱ ጎልማሣ ሚስተር ፕሪቪሌጅ ሙስፋሒሪ Privilege Musvanhiri ፣ የኦንላይን ጸሓፊ፣ፎቶግራፍ አንሺ የካሜራ ሰውና የራዲዮ ጋዜጠኛ ነው።

ትምህርቱንም በዋና ከተማው በሐረሬና በጀርመን አገር በበርሊን ከተማ የተከታተለ ነው። ለትልቁ የጀርመኑ የቴለቪዥን ጣቢያም ለ አ.አር.ዴ. እና ለአንደኛው የሰሜን ጀርመን ሳምንታዊ መጽሔት ለ ዲ ሳይት ያገለገለ ጋዜጠኛ ነው።

የፕረስ ነፃነት ያለገደብ

የፕረስ ነፃነት ያለገደብ

በጋዜጠኛነት ሙያው ዝምባቡዌ ውስጥ የሚያገኘው ገቢ ትንሽ በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ለምኑም አይበቃውም. እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ይሠራበት የነበረው ዝምባቡዌ ሜል Zimbabwe Mail የተባለው ዕለታዊ ጋዜጣ በቅርቡ በሩን ዘግቶ ቢሮውን ቆልፎ ከሚዲያው ዓለም ተሰናብቷል።

ጋዜጠኞች ተጠግተው ዕለታዊ ሥራቸውንና ሙያቸውን አለአንዳች ፍረሃቻ የሚያካሄዱበት ነፃ-ጋዜጣዎች በዚምባቡዌ የሉም።

በአሁኑ ሰዓት የእለት ቁርሱን….ጉርሱን እንዲሁም የሚጎነጫትን ወኃ ለማግኘትና ሕይወቱንም ለመግፋት ጋዜጠኛው ፕሪቪሌጅ ሙስፋሒሪ «ተንቀሳቃሽ የዜጎች የመንደር ራዲዮ ጣቢያ» የሚባለውን የቀበሌ ኑዋሪዎች በጋራ ተሰባስበው ተመካክረው የሚያዘጋጁትን ፕሮጄክት በአሠልጣኝነትና በአስተማሪነት እነሱን በመርዳት ላይ እሱ አሁን ይገኛል።
እንደ ሰማነው ይህ ፕሮጄክት በኔዘርላንዱ ገደብ የለሽ ነፃ- ፕሬስ በጎ አድራጎት ድርጅት በFree Press Unlimited Foundation የሚደገፍና የሚረዳ ነው።

ፕሪቪሌጅ ሙስቫንሂሪ/ይልማ ኃይለሚካኤል/ ማንተጋፍቶት ስለሺ

የዞን ዘጠኝ አንደኛ ዓመት የእሥር ጊዜ

DW.COM