በዓላትና የኃይል ፍጆታ | ጤና እና አካባቢ | DW | 06.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

በዓላትና የኃይል ፍጆታ

ዘመናዊዉ የአኗኗር ስልት በቴክኒዎሎጂ እየተረዳ ረዥም ጊዜ የሚፈጁ ተግባራትን በአጭር ጊዜና በፍጥነት ማከናወን ማስቻሉ በበጎ ጎን የሚነሳለት ጉዳይ ነዉ።

default

ያም ሆኖ ይኸዉ ዘመናዊ ስልት እንከንም እንደማያጣ የሚታይና የሚነገርለት ጉዳይ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ የቤት ባልትናዉ የሚጠይቀዉ ጊዜና አቅም እንዲሁም ለሂደቱ የሚዉለዉ ተጨማሪ የኃይል ፍጆታ ሲታሰብ እንደዉ ባይበላስ ሊያስብል ከሚችል ሙግት ቢያደርስ አይገርምም። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ አንድ የአካባቢ ተፈጥሮ ጥበቃ ባለሙያ ከአራት ሰዓታት በላይ በመብሰል ሂደት ጊዜ የሚወስዱ የባህል ምግቦች የኃይል አጠቃቀም ብክነት ተጨምሮባቸዉ ለደን መመናመን አስተዋፅኦ ያደርጋሉ ባይናቸዉ። አነሰም በዛም አመት በዓል መድረሱን ከግምት አስገብቶ የዕለቱ ጤናና አካባቢ ትኩረት ነዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ