በዓለማችን የተስፋፋው የሞት ቅጣት | ዓለም | DW | 28.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

በዓለማችን የተስፋፋው የሞት ቅጣት

ድርጅቱ እንደሚለው በዚሁ ዓመት በዓለማችን በአጠቃላይ 778 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል ። በድርጅቱ መግለጫ መሠረት በይፋ ከተፈፀሙ ከእነዚህ ቅጣቶች በተጨማሪ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቻይና በድብቅ በሞት ተቀጥተዋል ።

Symbolbild Todesstrafe

በጎርጎሮሳውያኑ 2013 ዓም በዓለማችን በሞት የተቀጡ ሰዎች ቁጥር ከቀዳሚዉ ዓመት 2012 ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ እንደነበረ ተዘገበ ። ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትናንት ባወጣው ዘገባ በ2013 በሞት የተቀጡ ሰዎች ቁጥር በ15 በመቶ ጨምሯል ። ለዚህም ድርጅቱ በምክንያትነት ያቀረበው በዓመቱ ኢራን፤ በኢራቅና ሳውዲ አረቢያ በሞት የቀጧቸዉ ሰዎች ቁጥር ማደጉ ነው ። ድርጅቱ እንደሚለው በዚሁ ዓመት በዓለማችን በአጠቃላይ 778 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል ። በድርጅቱ መግለጫ መሠረት በይፋ ከተፈፀሙ ከእነዚህ ቅጣቶች በተጨማሪ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቻይና በድብቅ በሞት ተቀጥተዋል ። የዶቼቬለው Michael Gessat የዘገበውን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አጠናቅሮታል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic