«በዓለማችን የሞት ቅጣት ብይን ቀንሷል» አምነስቲ | ዓለም | DW | 12.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

«በዓለማችን የሞት ቅጣት ብይን ቀንሷል» አምነስቲ

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ዘገባ በጎርጎሮሳዊው 2017 በዓለማችን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን ገለፀ። ድርጅቱ ጥቂት ተስፋ መሰነቁን ባንፀባረቀበት በዚህ ዘገባዉ በጎርጎረሳዊዉ 2017 በዓለም በሞት ቅጣት ብይን የሞተዉ ሰዉ ቁጥር ከካቻምናዉ ቀንሷል ብሎአል።   

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:36

የሞት ቅጣት ወንጀለኞችን ከድርጊታቸዉ ነፃ አያደርግም።

 

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ዘገባ በጎርጎሮሳዊው 2017 በዓለማችን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን ገለፀ። ድርጅቱ ጥቂት ተስፋ መሰነቁን ባንፀባረቀበት በዚህ ዘገባዉ በጎርጎረሳዊዉ 2017 በዓለም በሞት ቅጣት ብይን የሞተዉ ሰዉ ቁጥር ከካቻምናዉ ቀንሷል ብሎአል።    

በ 2017 በዓለማችን የሞት ቅጣት ፍርድ የተበየነባቸውና የሞት ቅጣት የተፈፀመባቸዉ ሰዎች ቁጥር ከካቻምናዉ ሲነፃፀር በጥቂቱም ቢሆን መቀነሱን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል። ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዓመታዊ ዘገባ እንዳለው በጎርጎሮሳዊው 2017 በዓለማችን 993 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል። እንደ አምነስቲ ገለፃ ይህ ቁጥር ከካቻምናዉ ጋር ሲነፃፀር የሞት ቅጣት በዓለማችን በ 4 % በመቶ ቀንሷል። በአምነስቲ ኢንተርናሽናል፤

በሃገራት የሚፈፀሙ የሞት ቅጣት ብይኖችን የሚከታተሉት ተመራማሪ ኦሉዋቶሲን ፖፓላ እደሚሉት፤ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነፃጸር ከፍተኛ የሚባል የሞት ቅጣት የሚፈጽሙት  ኢራን፤ ስዑድ አረብያ፤ እራቅና ፓኪስታንን መሆናቸውን ያስረዳሉ። እንድያም ሆኖ በነዚህ ሃገራት በጎርጎረሳዉያኑ 2017 አነስተኛ የሞት ቅጣት ብይን መተላለፉን ገጿል።   

«በአጠቃላይ በዓለም ዙርያ የሞት ቅጣት መቀነሱ በአመዛኙ በ3 አገራት ከተመዘገበው የቀነሰ የሞት ቅጣት ቁጥር ጋር የተያያዘ ነው። እነዚህ ሀገራትም ኢራን ሳዑዲ አረብያ እና ፓኪስታን ናቸው። ሆኖም የሞት ቅጣት የቀነሰው በአንድ ምክንያት ነው ብሎ መደምደም አይቻልም። ለምሳሌ በኢራን  በግድያ ወንጀል ምክንያት ይልቅ የሞት ቅጣት የተፈፀመባቸው ቁጥር በአደንዛዥ እፅ በሞት ከተቀጡት ይበልጣል። በፓኪስታን እና ስዑድ አረብያ ቀነሰ የተባለበትን ምክንያት ደግሞ ይህ ነዉ ብሎ በዉል መግለፅ አስቸጋሪ ይሆናል። ምክንያቱም በእነዚህ ሃገራት ዉስጥ አሁንም የሚፈፀመዉ የሞት ቅጣት በቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ ነዉ ። እንዲያም ሆኖ አቻምና 306 አምና ደግሞ ይህ ቁጥር ቀንሶ 158 ሰዎች የሞት ቅጣት ተፈፅሞባቸዋል»

በዘገባዊ በስዑድ አረብያ አሁንም የሞት ቅጣት ብይን ቁጥሩ እንዳል ቀነሰ ተመልክቶአል። እንደ አምነስቲ በግብፅ የሚታየዉ የሞት ቅጣት በጥቂቱም ቢሆን መቀነሱ ነዉ የተገለፀዉ። በኢራን የሞት  ቅጣት ብይን ቁጥር መቀነስ ምክንያት ለምሳሌ በሃገሪቱ የተካሄደዉ የሕግ ማሻሻይ እንደሆን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተመራማሪ ኦሉዋቶዊን ፖልላላ ገልፀዋል። ባለፈዉ የፈረንጆቹ ዓመት ከፍተኛ ተቃዉሞና ያለመረጋጋት በታየባት ኢራቅ 11 % የሞት ቅጣት ተፈፅሞአል ይህ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ፤ እምብዛም የሞት ቅጣት ተፈፃሚ እንዳልሆነ ይጠቁማል።  በፓኪስታን እንደባለፉት ዓመታት ሁሉ የሞት ቅጣት ብይን ተግባራዊ ተደርጎአል። እንደ አምነስቲ ዘገባ በለፈዉ ዓመት በ 23 የዓለም ሃገራት ዉስጥ የሞት ቅጣት ብይን ተፈፅሞአል። ባህሪን ክዊት እንዲሁም በአረብ ኤምሪት እና በዮርዳኖስ በአለፈዉ ዓመት የተፈጸመዉ የሞት ቅጣት ብይን እጅግ ማሽቆልቆሉ የሃገራቱ ዝርዝር መረጃ ያሳያል። የሞት ቅጣት ብይን  በሃገራቱ በግልፅ የተነገረ የታየ ነው። በሌላ በኩል ዉስጥ ዉስጡን የሚፈፀሙ ግን በግልጽ የማይነገሩ አልያም የማይሰሙ የሞት ቅጣቶች እንዳሉ ድርጅቱ አስታዉቋል።  

አምነስቲ  ከሰሃራ በታች በሚገኙ ሃገራት የታየዉ ለዉጥ አስደሳች ነዉ ሲል ባወጣዉ መረጃዉ ጊኒ የሞት ቅጣት ብይንን መሻርዋን ጋምቢያም የሞት ቅጣት ብይንን ለመሻር እንቅስቃሴ ጀምራ ምናልባትም ዳግም ለሞት ቅጣት ብይንን ለመፈፀም ሌላ ርምጃን ሳትጀምር እንዳልቀረች ተመራማሪዉ ተናግረዋል።  በ2017 ቻይና ምን ያህል ሰዎች በሞት እንደቀጣች በግልጽ  ያስቀመጠችዉ ነገር የለም። በዓለማችን የሞት ቅጣት ከሚፈፀምባቸው ሀገራት አንዷ በሆነችው በቻይና ወደፊት በሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሞት ቅጣት ሊፈፀምባቸው ይችላል  የሚል ጥርጣሬ እንዳለው አምነስቲ ገልጾአል።  

 የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶንዮ ጉተረስ የአምነስቲን ዘገባ መነሻ አድርገው በሰጡት አስተያየት የሞት ቅጣት ብይን አንድን ወንጀለኛ ሊሰራዉ ካሰበዉ ወንጀል አያስጥልም ሲሉ ተናግረዋል። የአምነስቲ ተመራማሪ ኦሉዋቶዊን ፖልላላም ይህንኑ ነዉ የደገሙት፤

«የሞት ቅጣትን መፈፀም ወንጀለኞችን ከድርጊታቸዉ ነፃ አያደርግም ። የሞት ቅጣት፤ ወንጀል የሚፈፅሙን አስፈራርቶና አስደንግጦ ከሚሰሩት ወንጀል ያስጥላል የሚል ይህ ነዉ የሚባል አሳማኝ ማረጋገጫም የለም። ለምሳሌ የሞት ቅጣትን የሚደነግገዉን ሕግ ከሻሩ ሃገራት መካከል ካናዳን ማየት ይቻላል።  በካናዳ በጎርጎሮሳዊው 2016 የተፈፀሙ ግድያዎች መጠን ሀገሪቱ የሞት ቅጣት ባነሳችበት በ1976 ከተፈፀሙት በግማሽ ያነሰ ነው።»

በዓለም ዙርያ በጎርጎረሳዉያኑ 2017 ዓም በሞት የተቀጣው ሰው ቁጥር መቀነሱን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ወሳኝ ለውጥ የታየበት ሲል አስታዉቋል።  

አዜብ ታደሰ/ ክላዉስ ዳህማን

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች