በውቅያኖስ ውሃ፣ ምድረ-በዳን፣ ምድረ-ገነት ማድረግ፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 24.06.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

በውቅያኖስ ውሃ፣ ምድረ-በዳን፣ ምድረ-ገነት ማድረግ፣

በዓለም ዙሪያ ፣ በውሃ ይበልጥ የሚጠቀመው ፣ የግብርናው ዘርፍ ነው። ይሁን እንጂ፣ ንፁህ የወንዝ ውሃ መጠን እየቀነሰ፣ እየተበከለ፣ እየጠፋም በሚሄድበት ዘመን፣ አማራጩን ብልሃት መሻት እጅጉን ይበጃል።

default

የወደፊቱ የምድረ በዳ ተስፋ፣ ተጣርቶ ሊቀርብ የሚችለው ጨዋማ የውቅያኖስ ውሃ፣

ታዲያ፣ አንድ እንግሊዛዊ ተመራማሪ፣ የአትክልት ችግኝ ማፍያ የመስታውት ቤቶችን፣ ከውቅያኖስ በቧንቧ በሚጠለፍ ውሃ፣ ልምላሜ-በልምላሜ እንዲሆኑ ማብቃታቸው፣ ምድረ -በዳ ቀመስ ለሆኑ አገሮች ሠናይ ዜናም ሆነ ብሥራት ሳይሆን አልቀረም። ተጣርቶ የሚቀርበው የውቅያኖስም ሆነ ጨው የበዛበት ውሃ የሚሰጠው ጠቀሜታ ተደራራቢ መሆኑ የሚታበል አይደለም።

መርኀ-ግብሩና አሠራሩ ቀላል ነው። ፀሐይ፣ ውቅያኖስን ታሞቃለች። የባህሩ ውሃ፣ እየተነነ ወደ አየር ይወጣና በዚያ ከቀዘቀዘ በኋላ፣ ርዶ ደመና ይፈጥራል። በኋላም፣ ዝናም ሆኖ ሲውርድ የጨውነት ጣዕም አይኖረውም። የብሪታንያው ተወላጅ ቻርሊ ፓተን፣ በዚሁ የተፈጥሮ ህግ አካሄድ ረገድ ነው የመስታውት ቤቶችን የሚያስጌጡት። ፎልከር ማርሴክ በዚህ ዙሪያ አጠር ያለ ጽሑፍ አቅርቧል። ተክሌ የኋላ አጠናቅሮታል።

ተክሌ የኋላ፣

ሒሩት መለሰ፣