1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን አስከፊ ገጽታ

ዓርብ፣ የካቲት 15 2011

ኢትዮጵያውያን ከሀገር ከወገናቸው ርቀው በውጭው ዓለም ሲኖሩ ከሚያሳልፏቸው የሕይወት ውጣ ውረዶች ሌላ ሀገር ቤት የሚገኙ ወገኖቻቸው የማይረዱላቸው ጥቂት የማይባሉ አሳዛኝ ገጠመኞችን ያሳልፋሉ።

https://p.dw.com/p/3DrtA
Trauerfeier und abschied in London von äthiopischen Gemeinde
ምስል DW/H. Demisse

መፍትሄ ለማግኘት በማሕበር አልያም በቤተ-እምነቶች አንድነታቸዉን፣ ባህላቸዉን ማጠናከር ይኖርባቸዋል

ዋናው እና ብዙዎችን የሚያስደነግጥ የሚያሳዝነው ድንገት ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩበት ወቅት የሚከሰተው ነው። እንዲህ ባለው አጋጣሚ አንዳንዶች ህልፈተ ሕይወታቸው እንኳ የሚታወቀው ውሎ አድሮ አለያም ሰንብቶ የሚሆንበት ጊዜ አለ። ከሰሞኑንም ብሪታንያ የሚገኙ ወገኖችን እንዲህ ያለው አጋጣሚ ሀዘን ብቻ ሳይሆን ድንጋጤንም አስከትሎባቸዋል። ይህ አጋጣሚ ታዲያ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮያውያን ለሕይወታቸው አስከፊ ገጽታዎች መፍትሄ ለማግኘት በማሕበር አልያም በቤተ-እምነቶች አንድነታቸዉን፣ ባህላቸዉን ማጠናከር ይኖርባቸዋል የሚል ማሳሰቢያን አስከትሏል። የለንደኗ ዘጋቢያችን ሃና ደምሴ ዝርዝር ታሪኩን እንደሚከተለው አጠናቅራ ልካልናለች። 
ሃና ደምሴ
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ