በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የመድረክ መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 23.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የመድረክ መግለጫ

መድረክ በዚሁ መግለጫው በአወዛጋቢው የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ እቅድ መንስኤ በኦሮምያ በተነሱ ተቃውሞዎች በዜጎች ላይ ለደረሰ ሞት እንዲሁም ለወደመው ንብረት ተጠያቂ የሆኑ ለፍርድ እንዲቀርቡ ለመንግሥት ጥሪ አስተላልፏል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:24
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:24 ደቂቃ

የመድረክ መግለጫ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል ።መድረክ በዚሁ መግለጫው በአወዛጋቢው የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ እቅድ መንስኤ በኦሮምያ በተነሱ ተቃውሞዎች በዜጎች ላይ ለደረሰ ሞት እንዲሁም ለወደመው ንብረት ተጠያቂ የሆኑ ለፍርድ እንዲቀርቡ ለመንግሥት ጥሪ አስተላልፏል ።መድረክ ከሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የፊታችን እሁድ አዲስ አበባ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ቢጠይቅም ሰልፉን ማካሄድ እንደማይቻል መንግሥት መልስ እንደሰጠውም አስታውቋል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic