በወሎ ማጅራት ገትር መሰል በሽታ የሰው ህይወት ማጥፋቱ | ኢትዮጵያ | DW | 28.07.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በወሎ ማጅራት ገትር መሰል በሽታ የሰው ህይወት ማጥፋቱ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ቃሎ ወረዳ ተከስቶ ምንነቱ በውል ባልታወቀ ማጅራት ገትር መሰል በሽታ ሀያ ሰዎች መሞታቸውን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታወቀ።

default

ሚንስቴሩ እንዳስረዳው፡ በሶስት ቀበሌዎች የተከሰተው ይኸው ወረርስኝ ወደሌላ አካባቢ እንዳይስፋፋ ግብረ ኃይል አቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ ነው። የተመድ የሰብዓዊ ርዳታ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት፡ በምህጻሩ ኦቻም ወረርሽኙ ከታየባቸው አካባቢዎች የተወሰደው ናሙና በሽታው በርግት ማጅራት ገትር መሆን አለመሆኑ እየተመረመረ መሆኑን አመልክቶዋል።

ታደሰ እንግዳው/አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ