በካይ ጋዞችን ለመቀነስ የግለሰብ ጥረት | ጤና እና አካባቢ | DW | 15.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

በካይ ጋዞችን ለመቀነስ የግለሰብ ጥረት

የአየር ንብረትን አስመልክቶ በተመድ የተካሄደ አንድ ጥናት ታዳሽ የኃይል ምንጭን መጠቀም አማራጭ እንደሌለዉ አመለከተ። በርሊን ላይ ይፋ የሆነዉ ይህ ጥናት በርካታ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ከተከማቸበት ከቅሪተ አፅም ከሚገኘዉ የኃይል ምንጭ ዓለም ባስቸኳይ ተላቆ ከባቢ አየርን ከጉዳት እንዲያድን ይማጸናል።

በሃገሮች መካከል የአየር ንብረት ለዉጥን ለመቆጣጠር ጥናት የሚያካሂደዉ መድረክ IPCC ሊቀመንበር ራጂንድራ ኩማር ፓቻዉሪ ርምጃ ለመዉሰድ በዘገየ ቁጥር ዓለም ብዙ መዘዝ እየተከተለዉ እንደሆነ አመልክተዋል።

«ረዥም ጊዜ በወሰድን ቁጥር የሚያስከፍለንም እንዲሁ ከፍተኛ ይሆናል። ማለቴ ይህ በጣም ግልፅ ነገር ነዉ። ከዚህ ሌላ ለማለት የምፈልገዉ አሁን መፍትሄ ለማምጣት የምናወጣዉ ያን ያህል ኤኮኖሚያችንን የሚያቃዉስ አይደለም። በአቅማችን የምንደርስበት ነዉ። ዓለም በጋራ ሊደርስበት የሚችል ነዉ። ነገር ግን የሙቀት መጠኑ ከሁለት ዲግሪ ሴልሺየስ እንዳይበልጥ በእርግጥ የምንፈልግ ከሆነ በፍጥነት መንቀሳቀስ አለብን ።»

ጥናቱ በቀጣይ የዓለም መንግስታት ብክለትን ለመቀነስ ለሚያደርጉት ድርድር እንደሚረዳ ነዉ የተገመተዉ። ሳይንቲስቶች በበኩላቸዉ የብክለት መጠኑን የመቀነሱ ርምጃ የማይሳካ ከሆነ እስከአሁን የሚታዩት የድርቅ፣ የባህር ወለል ከፍታና የሙቀት ማዕበል ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።

የዓለም የመቀት መጠን እንዲጨምር የሚያደርገዉን ከባቢ አየር በካይ አደገኛ ጋዝ ለመቀነስ የሚደረገዉ ጥረት መፋጠን እንደሚኖርበት በሃገሮች መካከል የአየር ንብረት ለዉጥን ለመቆጣጠር ጥናት የሚያካሂደዉ መድረክ IPCC አሳሰበ። የአየር ብክለቱ የሚያስከትለዉ ጠንቅ የምሁራን ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ግለሰብ ስጋት እየሆነየሄደ ይመስላል። ከመገናኛ ብዙሃን የሚሰሙት መረጃ ለፈጠራ እንዳነሳሳቸዉ የገለጹልን አቶ መስፍን ሥለሺ በግላቸዉ ባደረጉት ሙከራ ከፋብሪካ እየወጣ ከባቢ አየርን የሚበክለዉን ጋዝ ወደሌላ ጥቅም ለመለወጥ የሚያስችል መሳሪያ መፍጠር ችለዋል። ለፈጠራዉ የአእምሮ ባለቤትነት ምስርክ ወረቀት ያገኙ ሲሆን እሳቸዉ ናሙና የሚሉት ይህ ግኝታቸዉ በፋብሪካ ደረጃ ጥቅም ላይ እንዲዉል የአቅም ጉዳይ እንደያዛቸዉ ያስረዳሉ።

ዝርዝሩን ከድምፅ መረጃዉ ያገኙታል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic