በከሚሴ የተፈጠረዉ ግጭት | ኢትዮጵያ | DW | 04.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በከሚሴ የተፈጠረዉ ግጭት

በአማራ ክልል ስር በምትገኘዉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከሚሴ በሃርጡማ ፉርሴ ወረዳ በራሳሙሬ ቀበሌ ነዋሪዎችና በፀጥታ አስከባርዎች መካከል ግጭት መፈጠሩን የአከባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:29

ከሚሴ

በዚሁ ሰኞ በደረሰው ግጭት ፀጥታ አስከባሪዎች በአራት ቀበሌዎች ዉስጥ የሚገኙ «ቤቶችን እንዳቃጠሉም» ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ጸጥታ አስከባሪዎቹ እርምጃውን የወሰዱት ከነርሱ ጋር ስለተባበሯቸው ነው የምሉት።

ስማቸው እንዳይጠቅስ የጠየቁን ሌላ የሃርጡማ ፉርሴ ነዋሬ በሰኞው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን እና አንድ ግለሰብም ቆስሉ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተናግረዋል ። በዚሁ ግጭት አንድ የቀበሌ አስተዳደር ጉዳት እንደደረሰባቸውም  ለዶቼቬለ ገልጸዋል። 

እኝህ ግለሰብ የግጭቱን ምክንያት ሲያብራሩም፥ «የግጭቱ መነሻ ፀጥታ አስከባርዎች፣ የአሸባሪዎች አለማ ታራምዳላችሁ እንድሁም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባል ናቸሁ በማለት ግለሰቦችን ወስዶ በመግረፋቸዉ ነዉ። ወደ እስር ቤትም ወሰዶ በብሊታቸዉ ላይ ከባድ ነገር በማንጠልጠላቸዉና ይህን የመሳሰሉ ድርግት አካሄዶባቸዋል። በዝህም ምክንያት ህዝቡ የወሎ ማሂበረሰብ አንድነት የሚባል ድርጅት አቋቁሞ በተቻላቸዉ መጠን የመንግስት ፀጥታ አስከባሪ ወደ አከባቢው እንዳይገቡ በማድረጋቸዉ ነዉ ይህ ግጭት ልከሰት የቻለዉ።»

ይህ ድርጅት ማነዉ ያቋቋመዉ? እንዴትስ ልቋቋም ቻለ ስል ጠየኳቸዉ። «በዝህ ላይ ማህበረሰቡ ተስማምቶ ነዉ። ምክንያቱም በኦሮሚያ ዉስጥ ያሉት «ቄሮዎች» ችግር ስላጋጠማቸዉ የቀሩት የማህበረሰቡ አካል ወንድሞቻችን ተበድለዋል የሚል ስሜት ተስምቷቸዉ ነዉ። መንግስትም በሰላም ወቶ የሚገቡ ግለሰቦች ላይ የእስርና የማሰቃየት ርምጃ መዉሰድ ስጀምር መህበረሰቡ ወደ መሣርያ ማንሳት በመዞሩ ነዉ።»


ወታደሮች በ12 መክናዎች መቶ ሄጂራ፣ ራሳ፣ ዋጮታና ጃባስባ የተባሉት አራት ቀቤሌዎች እንዳቃጠሉና የአከባብዉ የቤት እንስሳትና ሌሎች  ንብረቶች መዉደሙን እኝህ ግለሰብ ይናገራሉ።
የከሚሴ አስተዳደር የህዝብ ግንኚነት ሃላፊ አቶ ሶሎሞን ካብትይመር ግን በማህበረሰቡና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል የተፈጠረ ግጭት የለም ይላሉ።

«በተባለዉ መልክ የተፈጠረ ግጭት የለም። እኔም አሁንም በሃርጡማ ወረዳ ነዉ ያለሁት። አሁን የልማት ኮንፊረንስ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ እንገኛለን። ኢሄ ነዉ ያለዉ አሁን። ቤት ተቃጠለ የምባለዉም አልሰማሁም፣ መረጃዉም የለኝም። ቅድም እንደነገርኩህ  አሁን ያለዉ ወደፊት አከባቢዉን መንከባከብ በተመለከተ እንዴት እንሂድበት የሚለዉ ላይ እየተወያየን ነዉ። ይሄ ነዉ ያለዉ። አስከዝህ ሰዓት ድረስ ከዚህ ለየት ያለ  ምንም መረጃ የለኝም።»

 
በአከባቢዉ የሚኖሩ ወይም ለአከባብዉ ቅርበት ያላቸው ደረሰ ስለተባለው ግጭት በዶቼቬለ ድረ ገፅ ላይ አስተያየታቸዉን አጋርተውናል።  የከሚሴ አካባቢ ነዋር መሆናቸዉን ገልጸው «እኛ ጋር ፍፁም ሰላም ነው። ኬሚሴ ዛሬም ነገም የሰላም መዲና ናት» ያሉ ሲኖሩ፣ ሌሎች ደግሞ «አሁን እዛው ነኝ። የታጠቀ ሠራዊት ልጆቻችሁን አምጡ ብለው የህዝብ ቤቶችን እያቃጠሉ ነው፣ ያሳዝናል» ስሉ አስተያየታቸዉን ሰንዝረዋል።

መርጋ ዮናስ

ሕሩት መለሰ

 

Audios and videos on the topic