በኦሮሚያ የተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ አንደኛ ዓመቱ | ኢትዮጵያ | DW | 11.11.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በኦሮሚያ የተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ አንደኛ ዓመቱ

በኦሮሚያ ክልል የተቀስቅሰዉ ተቃዉሞ ነገ አንድ ዓመቱን ይደፍናል። ከህዳር 2008 ዓ/ም በፊትም በክልሉ ተቃዉሞዎች ቢኖሩም ያለፈዉ አንድ ዓመት ያክል ግን ተከታታይና ጠንካራ አልነበረም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:21
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:21 ደቂቃ

ተቃዉሞ በኦሮሚያ

ዘገቦች እንደሚጠቁሙት አምና ሕዳር የነገ ዕለት ተቃዉሞዉ የተጀመረዉ ከአዲስ አበባ 55 ኪሎ ሜትር ርቃ  በምትገኘዉ በጊንጪ ከተማ ነበር።የከተማዋ ነዋርዎች አደባባይ የወጡት መንግስት በልማት ስም በአከባቢዉ የሚገኘዉን የጭልሞ ጫካን ማስመንጠሩን  በመቃወም ነበር። ከጫካዉ መመንጠር በተጨማሪ መንግስት ለልማት ይጠቅማል ብሎ ይዞ የወጣዉ የአድስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን የተቃዉሞዉን ጥያቄ በዋናነት ያቀጣጠለ መሆኑን ይታወሳል። ይህንን ተቃዉሞ ተከትሎ የብዙ ሰዉ ህወት ማለፉ ፣ ብዙ ሰዉ መታሰሩ፣ ንብረት መዉደሙና ብዙ ሰዎች ቀያቸዉን ጥለዉ መሰደዳቸዉን ስንዘገብ ነበር።

በመንግስት የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ሚንስቴር የህዝብ ግኑኝነት የሆኑት አቶ መሃመድ ሰይድ የተነሱት ጥያቄዎች በመልካም አስተዳዳደር እጦት የተከሰቱ ችግሮች  እና  ልማቱ ያመጣቸዉ ግን መሟላት ያለባቸዉ ፍላጎቶች በማነሳቸዉ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ።

በኦሮሚያ ክልል የነበረዉ ተቃዉሞ ከጭልሞ ጫካ  ከማስቴር ፕላኑ ጀርባ ብዙ ጥያቄዎች አሉ የሚሉት ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ በተቃዉሞዉ ተሳታፊ የነበሩት ግን ተቃራኒዉን ነዉ-የሚሉት።

የፖለትካ አቀንቃኝና ተቃዉሞዉን በቅርብ የተከታተሉት አቶ ገረሱ ቱፋ  ተቃዉሞዉ የሰዉ ነፍስ ለማለፍና ንብረቶች መጎዳታቸዉን ጠቅሶ፣ ግን ከዘ የበለጠ በኦሮሚያ ያለዉ የሰዉና የድሞክራትክ መብቶች ጥሳት የአለማቀፍ ትኩረትከፍት በበለጠ አግኝተዋል ይላሉ። 

መንግሥት ባለፍዉ ወር የደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሐገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ያመጣል ማለቱ ይታወሳል። አቶ ገረሱ እንደሚሉት ህዝብ ሲጠይቅ የነበረዉ አፋና፣ ግድያና ዘረፋዉ እንድቆም ነበር።«አዋጁ ግን የበለጠ እያጠናከረቸዉ  ነዉ» ይላሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ከደነገገ ወዲሕ ባለዉ አንድ ወር ዉስጥ ብቻ ከ11ሺሕ 600 በላይ ሰዎች ማሰሩን አምኗል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic