በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ወለጋው የጸጥታ ችግር እና የነዋሪዎች አቤቱታ | ኢትዮጵያ | DW | 23.05.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ወለጋው የጸጥታ ችግር እና የነዋሪዎች አቤቱታ

በምዕራብ ወለጋ ዞን ላሎ አሳቢ ወረዳ ከባለፈው ማክሰኞ አንስቶ የመንግስት በጸጥታ ሐይሎች በወሰዱት እርምጃ   በላሎ አሳቢ ስር በሚገኙ   በዋንጆ፣ኬላይ እና ጃርሶ ዳሞታ በተባሉ ስፍራዎች አምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን ላሎ አሳቢ ወረዳ ከባለፈው ማክሰኞ አንስቶ የመንግስት በጸጥታ ሐይሎች በወሰዱት እርምጃ   በላሎ አሳቢ ስር በሚገኙ   በዋንጆ፣ኬላይ እና ጃርሶ ዳሞታ በተባሉ ስፍራዎች አምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡  የንግድ ድርጅቶችን ጨምሮ አራት መኖሪያ ቤቶችም መቃጠላቸውን የአካባቢው  ነዋሪዎች አክለዋል፡፡ የምዐራብ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያ ኡመታ በበኩላቸው መንግስት በአካባቢው የህግ የበላይነት በማስከበር ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ የመንግሰት ጸጥታ ሀይሎች ህግን ከማስከበር ውጭ  በነዋሪው ላይ ያደረሱት ጉዳት እንደሌለም አክለዋል፡፡ በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች እና ሸማቂዎች መካካል በነበረው ግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ካለም አጣርተን ይፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

ከምዕራብ ወለጋ ዞን  ግምቢ ከተማ በ23 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚትገኘው ላሎ አሳቢ ወረዳ  ከሸማቂዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት የመንግስት ጸጥታ ሀይሎች በወረዳዋ ውስጥ በሚትገኙ ወንጆ በተባለች ስፋራ በተለያዩ የስራ ዘርፍ በተሰማሩ ግለሰቦች ላይ ጉዳት ማድረሱን ነዋሪቹ ገልጸዋል፡፡ አንድ ስማቸው እዲገለጽ ያልፈለጉ   በላሎ አሳቢ ወረዳ ዋንጆ ከተማ ነዋሪ  የመንግስት ጸጥታ ሀይሎች አደረሱት ባሉት ጥቃት በዋንጆ ከተማ ብቻ የሶስት የሰዎች ህይወት ሲያልፍ  አራት ቤቶች ደግሞ ተቃጥለዋል፡፡

…ድርጊቱ የተፈጸመው በምዕራብ ወለጋ ዞን ላሎ አሳቢ ወረዳ ዋንጆ ከተማ ነው፡፡ ታጠቃዎችን ትቀልባላቹ፣ደብቃቹል፣ መረጃም  አቀብላቹል ተብለው ሰላማዊ ሰው ማሰር፣ ቤት ማቃጠል እና በሰዎች ላይ ከፈተኛ ድብደባ አድረሰዋል፡፡ በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት አሳሳቢ በሆኔ ሁኔታ ውስጥ ነው ህዝቡ ያለው፡፡ ቤት ከተቃጠለበቸው መካከልም አቶ ደሳለኝ የተባሉ ሀኪም ሲሆኑ ክሊኒክም ነበራቸው፡፡ አቶ ከፍያለው እና አቶ ኪዳኑ  የሚባሉ ደግሞ በንግድ ስራ የተሰማራ ሲሆኑ ቤታቸውና ያለቸውን ቡና ሳይቀር  ተቃጥለባቸዋል፡፡ ከሞቱት መካካልም አቶ አበያ ቀልበሳ የእንስሳት ሀኪም የነበሩ  ፣አቶ ጋማችስ ጫላ፣  ወጣት መርጋ የተባለውም  የዋንጆ ከተማ  ነዋሪና  ተማሪ የነበረ ሲሆን kትናት በስቲያ  ስራተ ቀብራቸው ተፈጽመዋል፡፡ ፣ቃኖ ኤፍረም የተባለው ደግሞ  በላሎ አሳቢ ወረዳ ጃርሶ ዳሞታ ቀበሌ ነዋሪና ዘምድ ለመጠየቅ ወደ ዋንጆ እያቀና ባለበት ሰዓት ነበር የተገደለው፣   አንዲት ሴትም  ትናት ጠዋት በላሎ አሳቢ ኬላይ በተባለ ስፋራ ህይወቷ አልፏል ፡፡ ከሟቶቹ መካከል ቃኖ ኤፍረም የተባለው  የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛ ዓመት ተማሪ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

በከተማው በንግድ ስራ የተሰማሩ ሌላው የላሉ አሳቢ ነዋሪ  ሸማቂዎችን በገንዘብ ትደግፋለ ተብለው ቤታቸው እና ሱቃቸውም መቃጠሉን ተናግረዋል፡፡ ….  እኔ በንግድ ስራ ነው የሚተዳደረው ያለኝን ንብረት በሙሉ ነው ያቀጠሉብኝ ያለኝም ሱቅናና አንድ መኪና ሙሉ ንብረት አቃጥለዋል፡፡  ሰላማዊ ሰው ይደበድባሉ፣ሸኔ አለ እያሉ ያስረራራሉ ለዚህ ነው አካባቢውን ለቀን የሸሸነው፡፡ አሁን በርካታ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው ወደ ሌላ አካባቢ እየሸሹ ነው፡፡

የምዕራብ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ ኡመታ በዚው ጉዳይ ላይ በሰጡት ማብራሪያ  በአካባቢው የመንግስት ጸጥታ ሐይል ህግን ለማስከበር ከተሰማራ ረጅም ጊዜ እንደሆነ  ተናግረዋል፡፡ በአካባውም የተሰማራው የመንገስት ወታሮች  እና በሸማቂዎች መካካል በተለያዩ  ስፋራዎች ሰሞኑን  ግጭቶች እንደነበሩ የገለጹ ሲሆን ሰላማዊ ሰዎች በመንግስት ጸጥታ ሀይሎች  ስለመሞታቸውና ቤት ስለመቃጡም ደግሞ የተጣራ መረጃ የለንም ብለዋል፡፡  

በአካባቢው ያለውን ችግር ሰላማዊ መንገድ መፍታት ባለ መቻሉ መንግስት እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኃላፊው ጠቆመዋል፡፡ በምዕራብ ወለጋ እና ሌሎችም አካባቢዎች  ከዚህ ቀደም መንግስት በአካባው ሰላም ለማስፍን ሲባል ለሶስት ወራት ያህል  የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት አቋርጦ እንደነበረም የሚታወስ ነው፡፡  

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ