በእቃ መጫኛ አዉሮፕላን ተደብቆ ስዊድን የገባዉ ኢትዮጵያዊ | ኢትዮጵያ | DW | 08.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በእቃ መጫኛ አዉሮፕላን ተደብቆ ስዊድን የገባዉ ኢትዮጵያዊ

አንድ የ 27 ዓመት ኢትዮጵያዊ ወጣት በእቃ መጫኛ አውሮፕላን ውስጥ በመሆን ከ10 ሰዓት በረራ በሁዋላ ስዊድን መግባቱ ትናንት ታዉቋል። አዉሮፕላኑ እንደዉም ስዊድን ከመድረሱ አስቀድሞ ቬና አየር ጣብያ ለጥቂት ሰዓታት አርፎ እንደነበር ነዉ ዘገባዉ የምያሳየዉ።

ስለሰዉየዉ ማንነት እንዴት በዚህ መንገድ እዚህ ሊደርስ እንደቻለ ሚዲያዎች ያወጡት ሌላ ዝርዝር ዘገባ ባይኖርም ግለሰቡ መልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተዘግቦአል። ነሐሴ ወር ውስጥ አንድ የ 24 ዓመት የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ሰራተኛ እንደዚሁ በእቃ መጫኛ አውሮፕላን ውስጥ ሆኖ ስዊድን መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህ ትናንት ይፋ የሆነዉ ክስተት በ7 ወራት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። ምናልባት ከአዲስ አበባ ይህ አዲሱ መንገድ ሰዎችን በሕገ-ወጥ ማዘዋወርያ መንገድ ሳይሆን ሆኖ አይቀርም የሚል ጥያቄንም በብዞዎች ዘንድ አጭሮአል። በእቃ መጫኛ አዉሮፕላን ዉስጥ ተደብቆ ስዊድን ስለደረሰዉ ግለሰብ ሚዲያዎች ምን እየዘገቡ ነዉ። እዚህ ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት ስዊድን ስቶኮሆልም የሚገኘዉን ዘጋብያችንን ቲዮድሮስ ምሕረቱ አይቄዉ ነበር መልስ በመስጠት ይጀምራል።


ቴዮድሮስ ምሕረቱ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ