በእስር የሚገኙት የሲቪክ ማህበራት አባላት | ኢትዮጵያ | DW | 08.11.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በእስር የሚገኙት የሲቪክ ማህበራት አባላት

ምርጫ 97ትን ተከትሎ በተፈጠረዉ ዉዝግብ የአክሽን ኤድ ኢትዮጵያ ባልደረባ የሆኑት አቶ ዳንኤል በቀለና በማህበራዊ ፍትህ ላይ የሚሰራዉ Organization for Social Justice in Ethiopia የተሰኘዉ አገር በቀል ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ነፃነት ደምሴ መታሰራቸዉ ይታወሳል።

(ሻማ) የአምነስቲ አርማ

(ሻማ) የአምነስቲ አርማ

ሁለቱ የሲቪክ ተቋማት ባልደረቦች የታሰሩበትን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት የሻማ ማብራት ስርዓት ቤተሰቦች፤ ዘመድና ወዳጆች ዛሬ ማምሻዉን ሲያደርጉ፤ የስራ ባልደረቦቻቸዉ ግን ቀደም ብለዉ ረፋዱ ላይ አከናዉነዋል።