በእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭት የኃያላኑ አቋም | ዓለም | DW | 22.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

በእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭት የኃያላኑ አቋም

ሁለት ሣምንታትን ያስቆጠረው የእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭት አሁንም ድረስ አልተቋረጠም። በፍልስጥኤም በኩል ከ600 በላይ፣ ከእስራኤል ወገን ደግሞ ወደ 30 የሚጠጉ አይሁዶች መገደላቸው ተዘግቧል። የአረብ ሊግ እና የአውሮፓ ኅብረትን ጨምሮ የተመድ ብሎም ዩናይትድ ስቴትስ ግጭቱን ለማስቆም ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተጠቅሷል።

በእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭት የተመድ እና የዩናይትድ ስቴትስን አቋም አስመልክቶ ለዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ ቃለ-መጠይቅ አድርጌለት ነበር። አበበ የእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭት ምን መልክ እንደያዘ በማብራራት ይጀምራል።

እስራኤል የሐማስ ተዋጊዎች እየተሹለከለኩ ጥቃት የሚፈፅሙበትን የመሬት ውስጥ መተላለፊያ ደርምሼ ካልጨረስኩ የተኩስ አቁም ስምምነት የለም ብላለች። የሀማስ ተዋጊዎች በበኩላቸው ለ8 ዓመታት ጋዛ ውስጥ የተዘረጋው ማገጃ ይፍረስ፣ ከግብፅ ጋር የሚያዋስነን የራፋህ ድንበር ይከፈት እንዲሁም በእስራኤል ዳግም የታሰሩ የሐማስ ተዋጊዎች ይለቀቁ ሲሉ ቅድመ-ሁኔታ አስቀምጠዋል።

አበበ ፈለቀ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic