በኤርትራ የፕሪስ ነጻነት መጨለም | አፍሪቃ | DW | 11.01.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

በኤርትራ የፕሪስ ነጻነት መጨለም

ኤርትራዊ ጋዜጠኛ እንዲሁም በድራማ እና በግጥም ጽሁፎቹ ታዋቂነትን ያተረፈዉ ፍስሃዩ ዮሃንስ ልክ የዛሪ አመት የት እንደደረሰ ያልታወቀበትን ቀን በማሰብ በኔዘርላንድ የሚገኘዉ የኤርትራ ሰነዶች ምርምር እቀባ ድርጅት Ertriean Research & Documentation Center የፕሪስ ነጻነት በኤርትራ ጨልሟል በማለት የጹሁፍ መግለጫቸዉን ዛሪ ይፋ አድርጎአል

default

በኤርትራ የፕሪስ ነጻነት ተረግጦአል! ህዝቡም በአንባገነናዊዉ አስተዳደር እየተሰቃየ ነዉ! የሚሉትን ቀድሞ የፕሪዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የቅርብ አመካሪ የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት መቀመጫዉን በኔዘርላንድ ያደረገዉ ለኤርትራዉያን ዜጎች የሚሟገተዉ ድርጅት ዋና ጸሃፊን አቶ ኔጋሲ ጸጋይን አዜብ ታደሰ በስልክ አነጋግራ ይህን አጠናቅራለች