በኢ.ኦ.ተ.ቤ ተቋማት የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ጉዳይ | ኢትዮጵያ | DW | 10.09.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በኢ.ኦ.ተ.ቤ ተቋማት የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ጉዳይ

ሰልፉ የሚካሄደው በቤተክርስትያኒቱና በምዕመናኑ የሚደርሰው ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም ለመጠየቅ የቤተክርስቲያን መቃጠል፣ የካህናት መገደልና ሌሎች በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ለማውገዝ መሆኑን አስታውቀዋል።ሰልፉ ከኦሮምያ ቤተ-ክህነት ጋር እና ፤ ከባልደራስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለዉ አስታዉቀዋል።

«የመንግሥት አካላት ከሰልፉ በፊት የእንወያይ ጥያቄ አቅርበውልናል»አቶ ሰይፉ ዓለማየሁ

ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ አስር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የተለያዩ ተቋማት ለመስከረም አራት 2012 የታቀደዉን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያስተባብሩ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ገለፁ።ተቋማቱ በመግለጫቸዉ ሰልፉ የሚካሄደው በቤተክርስትያኒቱና በምዕመናኑ ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም ለመጠየቅ የቤተክርስቲያን መቃጠል፣ የካህናት መገደልና ሌሎች በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ለማውገዝ መሆኑን አስታውቋል። ይሁን እንጂ ሰላማዊ ሰልፉ ከኦሮምያ ቤተ-ክህነት ጋር እና ፤ ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ እስክንድር ነጋ ከሚመራዉ ባልደራስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለዉ አስታዉቀዋል። ጥያቄ ለመንግሥት አቅርበን የእንወያይ ጥያቄ ቀርቦልናል፤ የፊታችን አርብ መስከረም ሁለት ድጋሚ ዝርዝር መግለጫ እንሰጣለን ሲሉ አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታዋህዶ ቤተ ክርስትያን ተቋማት ለመስከረም አራት የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ካስተላለፉ በኋላ በአዉሮጳና ሰሜን አሜሪካ በእለቱ ተመሳሳይ ሰልፍ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር መግለጫውን ተከታትሏል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ 

Audios and videos on the topic