በኢትዮጵያ ግጭት፣ ተቃውሞ እና የመንግስት እርምጃዎች | ኢትዮጵያ | DW | 04.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ግጭት፣ ተቃውሞ እና የመንግስት እርምጃዎች

በኢትዮጵያ እሥረኞች መፈታት ከጀመሩ በኋላ ተቃውሞ እና ግጭት ጋብ ያለ መስሎ ነበር ።ሆኖም ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በተለይ ሰሜን ወሎ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች የተነሳው ግጭት አሁንም አለመርገቡ ነው የሚሰማው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 29:55

ውይይት፦ ግጭት ተቃውሞና የመንግስት እርምጃዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  «የተሻለ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት» በሚል ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት በፌደራል እና በክልል ተይዘው የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ እሥረኞች ተለቀዋል። እየተለቀቁም ነው። ሆኖም እርምጃው በዜጎችም በውጭ መንግሥታትም ተወድሶ ሳያበቃ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከሌሎች አካባቢዎች ጋር ሲነጻጸር አንጻራዊ ሰላም ነበረው በሚባለው በሰሜን ወሎ ወልድያ የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ አጎራባች ከተሞች ተዛምቶ የሰዎች ህይወት አልፏል፣ንብረት ወድሟል፤ በርካቶችም ታስረዋል።  የአማራ ክልል ችግሩን ለመፍታት ከወጣቶች ጋር መነጋገሩን ቢያሳውቅም ግጭቱ አለመርገቡን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እስከዚህ ሳምንት አጋማሽ ድረስ ሲዘግቡ ነበር። በግጭቱ በአካባቢው ከተሞች የንግድ የትራንስንስፓርት እና የሥራ እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለዋል። በኢትዮጵያ የቀጠለው ተቃውሞ እና ግጭት እንዲሁም የመንግስት እና የክልሎች ርምጃዎች የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው። 

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ

 

Audios and videos on the topic