በኢትዮጵያ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ አጠቃቀምና ግብይት | ጤና እና አካባቢ | DW | 13.08.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

በኢትዮጵያ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ አጠቃቀምና ግብይት

ከቅርብ አመታት ወዲህ በኢትዮጵያ በስፋት ከተዋወቁት የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች መካከል « ኤሜርጄንሲ ኮንትራሴፕቲቭ» ወይም ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ

የሚባሉት ይገኙበታል።በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በስፋት በሚሰራጩት በእንክብሎቹ አጠቃቀምና ግብይት ላይ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ የስነ-ተዋልዶ ጤና ባለሙያዎች ያሳስባሉ።በኢትዮጵያ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ የሚባሉትን የእነዚህን እንክብሎች አጠቃቀምና ግብይት በተመለከተ ችግሮች እንዳሉና ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል ።

ያልተጠበቀ ወሲባዊ ግንኙነትን፣ ሌላ የእርግዝና መከላከያዎች አስተማማኝነት በሚያጠራጥርበት ጊዜ ወይንም መደፈርን ተከትሎ ከሚወሰዱ የተለያዩ የእርግዝና መከላከያ መንገዶች መካከል የአስቸኳይ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች የሚባሉት ይገኙበታል። እነዚህ እንክብሎች ግንኑነት በተደረገ በ 72 ሰዓታት ውስጥ መወሰድ ሲገባቸው የሚወሰዱበት መጠን እንደ ኬሚካል ይዞታቸው ይለያያል። መከላከያዎቹን ለመውሰድ መዘግየት እርግዝና ሊያጋጥም የሚችልበትን ሁኔታ ይበልጥ እንዲጨምር

Gegen Abtreibung Mexico Stadt

ያደርጋል።የስነ-ተዋልዶ ጤና ባለሙያዋ ወይዘሪት ዮዲት ቦጋለ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ የሚባሉትን ከአንድ ጊዜ በላይ መጠቀም አይመከርም ይላሉ።የስነ-ተዋልዶ ጤና ባለሙያዋ አላስፈላጊ እርግዝናን የሚሸሹት የድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ የሚባሉት ተጠቃሚዎች አግልግሎቱ የሚተዋወቅበት መንገድም ሰለባ ናቸው ይላሉ።

የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መንግስተዓብ ወልደ አረጋይ ችግሩ መኖሩን አምነው መንግስት መፍትሄ ለመስጠት በሂደት ላይ ነው ይላሉ።

መድሃኒቱ የሚሸጥበትን መንገድ ተዘዋውረው የተመለከቱት ወይዘሪት ዮዲት ቦጋለ አገልግሎቱ ለተጠቃሚዎች የሚቀርብበት መንገድ በትኩረት ሊታይ ይገባል ሲሉ ይናገራሉ።

እሸቴ በቀለ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic