በኢትዮጵያ የግብርናዉ ክፍል የምርት እድገት አልተለየዉም ተባለ | ኢትዮጵያ | DW | 23.05.2022
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የግብርናዉ ክፍል የምርት እድገት አልተለየዉም ተባለ

በሰላም እጦት ፣ በግጭት፣ በድርቅ እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት እየፈተነ ያለው የኢትዮጵያ የግብርና ክፍል ኢኮኖሚ ከእነ ችግሮቹም ቢሆን የምርት እድገት ያልተለየው መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ተናገረ። ሚኒስቴሩ ይህ ዘገባ የትግራይ ክልልን እንደማይጨምር አውስቷል።

 

በሰላም እጦት ፣ በግጭት፣ በድርቅ እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት እየፈተነ ያለው የኢትዮጵያ የግብርና ክፍል ኢኮኖሚ ከእነ ችግሮቹም ቢሆን የምርት እድገት ያልተለየው መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ተናገረ። ሚኒስቴሩ የዘጠኝ ወራት የሥራ ክንውኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክር ቤት ለግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ ይህ ዘገባ የትግራይ ክልልን እንደማይጨምር አውስቷል።

660 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል ተሸፍኗል ያሉት የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሑሴን በግብርና ዘርፍ ባለሀብቶች እንዲለማ ታቅዶ የነበረ ሰፊ መሬት አንድም በሰላም እጦት ፣ በሌላ በኩል በብድር አቅርቦት ችግር ጦም ማደሩን ተናግረዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1.5 ቢሊዮን ዶላር ከግብርና ምርት ግብይት ተገኝቷል ያሉት ሚኒስትሩ አብዛኛው ገቢ ከቡና የተገኘ መሆኑንም ተናግረዋል።

አርሰው ሕዝብ ሲመግቡ የነበሩ አሁን በጦርነትና በግጭት ሳቢያ ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎች ወደ ቀደመ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic