በኢትዮጵያ የእስረኞች መፈታት | ኢትዮጵያ | DW | 10.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የእስረኞች መፈታት

በእነ አቡበከር አህመድ እና በእነ ኤሊያስ ከድር መዝገብ በጸረ-ሽብር ሕግ ተከሰው ተፈርዶባቸው ከነበሩት የሙስሊም መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ውስጥ 13ቱ ዛሬ ከእስር ቤት «በይቅርታ» መለቀቃቸው ተገለጠ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:56

የእስረኞች መፈታት

ከሙስሊም መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መካከል 13ቱ እስረኞች ሲፈቱ፤ ከእነ አቡበከር ጋር የታሠሩ አራት እስረኞች ግን አሁንም በእርስ ቤት እንደሚገኙ የእስረኞቹ ጠበቃ አዲስ መሐመድ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ጠበቃዋ፦ አቡበከር አህመድ፣ በድሩ ሑሴን፣ ካሚል ሸምሱ፣ ሙባረክ አደም፣ ሼህ መከተ ሙሔ፣ ኑሩ ቱርኪ፣ ሙራድ ሽኩር፣ ይሱፍ ጌታቸው ከቤተሰባቸው ጋር መቀላቀላቸውን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። ከዚህ በተጨማሪ ከነ ኤልያስ ከድር መዝገብ አብዱል መጂድ አብዱል ከሪም፣ ሙባረክ፣ ቶፊቅ መሐመድ እና መሪማ ሐያቱ ከእስር መፈታታቸውንም ጨምረው ገልጠዋል። በእነ አቡበከር መሐመድ የክስ መዝገብ ከተካተቱት መካከል ያልተፈቱ አራት ሰዎች እንደሚቀሩ ጠበቃ አክለዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic