በኢትዮጵያ የኢንቴርኔት ነፃነት ማሽቆልቆሉ | ኢትዮጵያ | DW | 15.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የኢንቴርኔት ነፃነት ማሽቆልቆሉ

በኢትዮጵያ በኢንቴርኔት ነፃነት ላይ በልዩ ልዩ መልኩ የተጣለው ገደብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን መቀመጫዉን አሜሪካ ያደረገዉ ፍሪደም ሃዉስ የተሰኘዉ የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት ትናንት በዘገባዉ አስታውቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:08

የኢንቴርኔት ነፃነት

መቀመጫዉን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገዉ ፍሪደም ሃዉስ የተሰኘዉ የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት በኢትዮጵያ የኢንቴርኔት ነፃነት ይዞታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣቱን ትላንት ይፋ ባደረገዉ ዘገባዉ አሳዉቀዋል። ፍርዳም ኦን ዘ ኔት 2017 በሚል የወጣዉ ይኽው ዘገባ የ65 አገራት አጠቃላይ የኢንቴርኔት ነፃነትን ለመመዘን ከዜሮ እስከ 30 ቁጥር ነፃ የሆኑ፣ ከ31 እስከ 60 በከፊል ነፃ  እንዲሁም ከ61 እስከ 100 ደግሞ የኢንቴርኔት ነፃነት የሌለባቸው አገራት በሚል መድቧቸዋል።

በዚህም መሰረት ቻይና የኢንቴርኔት ነፃነት የለባቸውም በተባሉ ሀገራት ተርታ 87ተኛ ደረጃ የተሰጣት ስሆን ኢትዮጵያና ሶርያ ደግሞ 86ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ይህም የኢንተርኔት አገልግሎትን ማገድ ፣ መልዕክቶች በኢንቴርኔት እንዳይሰራጩ መከልከል በዚህ ሂደትም የተጠቃሚዎቹን መብት መጣስ በአስደንጋጭ ሁኔታ መባባሱን የሚያሳይ መሆኑንን ድርጅቱ አስታውቋል።

ለዚህ መንሴዉ የሆነዉ ምንድነዉ? የለንደኑ «ቻታም ሃዉስ» የተባለው የፖለቲካ ጥናት ተቋም የአፍሪቃ ፕሮግራም ተባባሪ ተመራማሪ  ጀሳን ሞስል: «በኢትዮጵያ ዉስጥ ቴሌኮሙኒኬሼን ሴክቴሩ ነፃ አልሆንም። በአጠቃላይ አሁንም መንግስት በኤኮኖሚ ትልቅ ሚና ኢየተጫወተ ይገኛል፣ ኢሕአዴግም ዘርፉ ከመንግስት እጅ እንዳይወጣ ወስኗል። መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የተሌኮሙኒኬሼን መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ተሰማርተዋል፣ ግን የግል የተሌኮሙኒኬሼን አገልግሎት ሰጭዎች የሉም። ይህ ማለት ደግሞ ከሌሎች አጋሮች የበለጠ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ የኢንቴርኔት ግኑኝነቶች /connectivity/ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነፃጸር እያሽቆለቆለ እንዲሄድ አድርጓል።»

መንግስት የኢንቴርኔትን አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ በመያዝ ገቢ ከማግኘቱም በተጨማሪ መንግስትን የሚቃወሙ ድምፆችን ለማፈንም ይጠቀምበታል ይላሉ ጀሳን። እንደ ጃሳን በአገሪቱ ያሉ የኢንቴርኔት በተለይ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ተጠቃሚዎች  ለመንግስት ራስ ምታት ሆነውበታል። ምክንያቱንም እንዲህ ዘርዝረዋል፣ «ማህብራዊ መገናኛ ብዙሀን አገር ውስጥም ላሉት አክቲቪስቶችም ሆነ ዉጭ ላሉት ጋር ለመገኛኘትና ከአንድ የአገሪቱ አከባቢ የተገኘዉን መረጃ ከሌላዉ አከባቢ ጋር ለመለዋወጥ ትልቅ ሚና መጫወቱ ምንም ጥርጣሬ የለም።»

በጉዳዩ ላይ በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ገፅ ተሳታፊዎችን አወያይተን ነበር። ፊቃዱ ያደሳ የሚል የፌስቡክ ስም የያዙ አንድ ግለሰብ «ወይ ኢንተርኔት፣ የቀን ጅብ ቢባል ያንሰዋል፤ለዘያውም የተገደበ» ነዉ ስል ቢላሉል ሀበሽ በሚል ደግሞ በተለይ ከሁለት ወር ወዲህ የኢንቴርኔት አገልግሎቱ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነና ገንዘባቸዉን «ኢየበላ» እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

የኢንቴርኔት አጋልግሎት ዘገምተኛ በመሆኑ ገንዘባቸዉን ኢየጨረሰባቸዉ እንደሆነ ፣ ቴሌኮሙኒከሼን ሲጠየቅም መልስ እንደማይሰጥ በዋትስአፕ አስተያየት የላኩም አሉ።

የኢንቴርኔት አጋልግሎትን ማጋድ ማለት የትዉልዱን የእዉቀት ምንጭ እንደ መገደብ ይቆጠራል ያሉት ሌላ አስተያየት ሰጭ መንግስት «እኛን በረት ዉስጥ አስቀምጦናል ይላሉ»።

በቅርቡ ኢትዮጵያ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሀንን የሚገድብ ረቅቅ አዋጅ እያዘጋጀች ነዉ ተብሎ ቢወራም የመንግስት ባለስልጣናት ግን አስተባብለዋል።
ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል በፍሪደም ሃዉስ ዘገባ ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

ሂሩት መለሰ  

Audios and videos on the topic