በኢትዮጵያ የምግብ ርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር መቀነሱ | ኢትዮጵያ | DW | 03.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የምግብ ርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር መቀነሱ

በኢትዮጵያ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ተረጅዎች ቁጥር ከ10.2 ሚልዮን ወደ 5.6 ሚልዮን መውረዱን የኢትዮጵያ የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጥናት ይፋ አድርጓል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:10
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:10 ደቂቃ

የምግብ ርዳታ

በአገሪቱ በቆላማና አርብቶ አደር አከባቢ የዝናብ እጥረት በሰዎችና በእንስሳት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። ሃላፊው ለተረጂዎች ምን ዓይነት ድጋፎች እንደሚሰጡም ገልጸዋል።

እነዚህን 5.6 ሚልዮን ዜጎች ለመርዳት ለምግብ እና ምግብ ነክ ላልሆኑ ወጪዎች 921.9 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የሚናገሩት አቶ ደበበ ይህም ከኢትዮጵያ መንግስትና ከአጋር ድርጅቶች እንደሚገኝ ያስረዳሉ።

በአገሪቱ ተከስቶ የነበረዉን የድርቅም ሆነ የጎርፍ አደጋን የመከላከል ሥራ ሲያከናውኑ ከቆዩት አንዱ የተመድ የሰብዓዊ ርዳታዎች ማስተባበርያ ቢሮ በምህጻሩ /OCHA/ ነው ።  የ ኦቻ ምክትል ቃል አቀባይ ዬንስ ሌርኬ ለተፈጠረዉ አደጋ የመንግስት ምላሽ «በጣም የዘገየ» እንደነበረ ተናግረዋል፣ ግን በአለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች ተሳትፎ አደጋዉን ማቅለል ተችለዋል ይላሉ። አደገዉን ለመቋቋም ስለሚያስፈልገዉ የገንዘብ ርዳታ ሲናገሩም፣ «በኛ ርዳታና በመንግስት መሪነት ለአደገዉን ምላሽ ለመስጠት እቅዶች አሉ። ለምሳሌ ባለፈዉ ዓመት 1,6 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግ በእቅድ ተይዞ ነበር። በዚህ ዓመት ደግሞ ከባለፈዉ ዓመት በጣም ያነሰ 895 ሚሊዮን የአሜርካ ዶላር እንደሚያስፈልግ በእቅድ ተይዟል። ባለፈዉ ዓመት ከታቀደዉ ዉስጥ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ተሰብስቦ ለኢትዮጵያ መንግስት ተልኳል።»


የኢትዮጵያ መንግስት ጥናት ካካሄደ በኋላ የተረጅዎች ቁጥር ከ10,2 ሚሊዮን ወደ 5,6 ሚሊዮን ወርደዋል ማለቱን እንዴት ይመለከቱታል ብዬ አቶ ዬንስ ጠይቄአቸው ነበር፣ «በቁጡሩ ላይ ከመንግስት ጋር እንስማማለን። እኛም በጎሪጎረሳዊዉ አቆጣጠር በ2017 በአደጋዉ ለተጎዱትን 5.6 ሚሊዮን ሰዎች የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ርዳታዎችን ለመስጠት አቅደናል። ቁጥራቸው ከፍ ላለው ደግሞ ንጹህ የመጠጥ ዉሃ  ማቅረብና በድርቁ ግዜ እንስሳቶቻቸዉን ላጡት መልሰው እንዲቋቋሙ ለማቋቋም ርዳታዎች እየተሰጡ ነዉ።»


በቆላማና በአርብቶ አደር አከባቢ በተለይም በደቡብ ክልል 148,000 እስር መኖ፣ ለሶማሊ ክልል 30,000 እስር መኖና ለኦሮሚያ ክልል 50,000 እስር መኖ ኮሚሽኑ አየላከ መሆኑን አቶ ደበበ ይናገራሉ። 

መርጋ ዮናስ

ሕሩት መለሰ 


 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች